የሪህ በሽታ መንስኤዎች / Gout

ሪህ በአጥንት መገጣጠሚያዎች ላይ ከፍተኛ የሆነ ህመም የሚያስከትል የህመም ዓይነት ነው፡፡

ዩሪክ አሲድ በሰውነት ውስጥ በተፈጥሮ የሚገኝ ንጥረ ቅመም ሲሆን ይህ ንጥረ ቅመም በሰውነት ውስጥ በተወሰነ መጠን መገኘት ያለበትና በሽንት በኩል የሚወገድ ነው፡፡
ሆኖም ይህ ንጥረ ነገር በሰውነት ውስጥ ከሚፈለገው መጠን በላይ ሲሆን ሰውነታችን ለማስወገድ አቅም ያጣል፡፡
 በዚህን ጊዜ ካልሼም ፎስፊት ወደሚባል ጠጣር ንጥረ ነገርነት ተቀይረው ወደ መገጣጠሚያ ቦታዎች ይሰበሰባሉ፡፡
 ከዚህም ሌላ የተከማቸው ዩሪክ አሲድ በኩላሊት ውስጥ እና በሽንት ማመላለሻ መስመሮች ውስጥ በመዝቀጥ የኩላሊት ጠጠር ሊፈጥር ይችላል ፡፡

ለሪህ የጤና ችግር በመንስኤነት የሚገለፁ የተለያዩ ጉዳዮች አሉ፡፡ በዋና ዋና የሚባሉት የሚከተሉት ናቸው፡፡
• የዕድሜ መጨመር
• በሰውነት ውስጥ ከሚፈለገው በላይ የንጥረ ነገሮች መፈጠርና መከማቸት
• በሽታ አምጪ ተህዋሲያን አማካኝ /infection/
• ከቤተሰብ መካከል የጤና ችግሩ ካለ በዘር የመተላለፍ ዕድል ይኖረዋል
• ምክንያታቸው በውል የማይታወቅ ጉዳዮች /idiopathic/
ተጋላጭነተወዎን የሚጨምሩ ነገሮች
• ለሪህ ከሚያጋልጡ ምክንያቶች መካከል ከአኗኗር ዘይቤ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ለምሳሌ በአመጋገብ ስርዓት ውስጥ ቀይ ሥጋ፣ ጉበት ኩላሊትና የጭንቅላት ስጋን አዘውትሮ መመገብ እንዲሁም አልኮል መጠጣት ለሪህ በሽታ ተጋላጭ የመሆን ዕድልን ያሰፋሉ፡፡ከላይ ከተገለፁት በተጨማሪ
• የሰውነት ክብደት መጨመር፣
• በቁጥጥር ስር ያልዋለ ደም ግፊት፣
• ውሃ በብዛት ያለመጠጣት፣
• የኩላሊት በሽታና ለተለያዩ በሽታዎች የሚሰጡ መድሃኒቶች ለሪህ በሽታ ተጋላጭ ያደርጋሉ፡፡

የህመሙ ምልክቶች
• ከትንሽ የጣት ጫፍ እስከ ትላልቆቹ የሰውነት ክፍሎች አካባቢያሉ መገጣጠሚያ ቦታዎች ያብጣሉ
• የሰውነት ትኩሳት መከሰት
• ከቁርጥማት ጀምሮ መላ መገጣጠሚያ ቦታዎችን በመንካት እስከሚቸግር ድረስ ህመም
• ከፍተኛ ስቃይ ያለው ህመም
• መገጣጠሚያ አካባቢዎች በተለይ መልኩ መቅላት
• በመገጣጠሚያ አካባቢዎች የማቃጠል ሁኔታ ይከሰታል
• የጡንቻ መዛል በተለይ ጠዋት ጠዋት እጅና እግርን ለማንቀሳቀስ መቸገር ይኖራል
• የጤና ችግሩ ከሁለት ሳምንት በላይ ከቆየ በመገጣጠሚያ ቦታዎች ጠጣርየሆኑ ነገሮች ይፈጠራሉ
• በዓይን፣ በቆዳ፣ በልብና በሌሎችም አካባቢዎች የህመም ስሜቶች ይከሰታሉ
• ቁርጥማት
• በዓይን፣ በቆዳ፣ በልብና በሌሎችም አካባቢዎች የህመም ስሜቶች ይከሰታሉ፡፡
ህክምና
አንድ ሰው ለመጀመሪያ ወይም በተደጋጋሚ ጊዜ የሪህ በሽታ ከተከሰተበት ከፍተኛ ስቃይ ይኖረዋል፡፡የመጀመሪያው የህክምና ስቃዩን ለማስታገስ የሚያስችል መድሃኒቶች ይታዘዛሉ ፡፡
በዚህ ረገድ Non-Steroid Anti-Inflamaty drugs /Nsaids/ በቀዳሚነት ይጠቀሳሉ፡፡
በእነዚህ መድሃኒቶች ለውጥ ካልመጣ Corticoid Steroids የሚባሉ መድሃኒቶችን በመርፌ ወይም በሚዋጥ መልክ ይሰጣል ፡፡
 እነዚህ መድሃኒቶች የህመም ስቃይን ከማቃለል በተጨማሪ መገጣጠሚያ ከጥቅም ውጭ እንዳይሆን ለጊዜው ፋታ ይሰጣሉ፡፡
ሌላኛው የህክምና ዘዴ Uric acid ከሰውነት ውስጥ እንዲቀንስ ማድረግ የሚችሉ መድሃኒቶች ነው፡፡
በእነዚህ መድሃኒቶች ለማከም ጥረት ይደረጋል፡፡
 እጅና እግር መንቀሳቀስ ካቆመ በቀዶ ህክምና እንዲስተካከል ይደረጋል፡፡