ለብዙ ዓመታት ሰዎች በተለያዩ ሃይማኖት ውስጥ ሆነው ፆምን መንፈሳዊና ባህላዊ በረከትን በመሻት ሲከውኑት ቆይተዋል፡፡ በቅርብ አመታት ወዲህ ደግሞ ሳይንቲስቶችና ተመራማሪዎች ፆም በርካታ የጤና ትሩፋቶች እንዳሉት እየተናገሩ ነው፡፡ ከምግብና መጠጥ ለተወሰኑ ሰዓታት መከልከል ዛሬ ላይ ለተለያዩ ሕመሞች ፈውስን እስከ መስጠት ላይ ተደርሷል፡፡ እኛም 10ሩን የፆም የጤና በረከቶች እነሆ
#ፆም ክብደት ይቀንሳል፡-
ፆም በፍጥነትና የተሻለ የሰውነት ክብደትን ለመቀነስ አማራጭ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ ምግብ ስንመገብ ሰውነታችን ኃይል ያገኛል፡፡ ተጨማሪ ምግብ ስንመገብ ሰውነታችን ምግቡን በቅባት መልክ አዘጋጅቶ ወደ ፊት እንድንጠቀምበት ያደርጋል፡፡ በፆም ጊዜ ግን የበላነው ምግብ ተፈጨቶ በቀጥታ ወደ ኃይልነት ስለሚለወጥ አይከማችም በዚህ የተነሳ ተጨማሪ ኃይል እንኳን ቢያስፈልገን በፊት የተከማቸውን ቅባት በመጠቅም የሰውነት ክብደታችን እንዲቀንስ ያደርጋል፡፡
ረጅም ዕድሜ ለመኖር ፆም ወሳኝነት አለው፡-ዕድሜያችን እየገፋ ሲመጣ የጡንቻ ሕዋሳት እና አጠቃላይ የሰውነት ሕዋሳችን በማርጀት ምክንያት ተግባራቸውን በአግባቡ እንዳይወጡ ያደርጋል፡፡ በተደጋጋሚ የምንፆም ከሆነ ግን ሕዋሳቶተቻች እንዲያገግሙና ተግባራቸውንም በፍጥነት እንዲወጡ በማገዝ እርጅናን በማዘግየት ረጅም ዕድሜ እንድንኖር ይረዳል፡፡
ፆም መርዘማ ነገሮችን ያስወግዳል፡-
በተለያየ ወቅት ከምግብ ጋር ወደ ሰውታችን ውስጥ የገቡ ማጣፈጫና አደገኛ መርዞች በቅባት መልክ በሰውነታችን ውስጥ ይከማቻሉ፡፡ እነዚህን አደጋኛ መርዞች በጉበት አማካኝነት በፆም ጊዜ እንዲወገዱና ቅባቱ ለሰውነታችን አገልግሎት እንዲሰጥ በአዕምሮአችን ትዕዛዝ ይሰጣል፡፡ በዚህም የተነሳ ኩላሊታችንና ሌሎች የሰውነታችን ክፍሎች ከመርዛማ ነገሮች በቀላሉ ይነፃሉ፡፡
የምግብ መቃጠለን ያፋጥናል፡-
በፆም ወቅት ጨጓራችን የተወሰነ ሰዓት ስለሚያርፍ ከፆም በኃላ ምግብ በአግባቡ ተፈጭቶ በፍጥነት ወደ ኃይልነት ለመቀየር ዕድል ይፈጥራል፡፡
የአዕምሮ ተግባርን ያሳድጋል፡-
ፆም በአጠቃላይ ለሰውነታችን ከሚሰጠው ጥቅም በተጨማሪ አእምሮ ስራውን በአግባቡ እንዲወጣ ያግዛል፡፡ ፆም ኒሮ ትራፊክ ፋክተር የተሰኘውን ሆርሞን ምርት ይጨምራል፡፡ የዚህ ሆርሞን መጨመር የአእምሮ ሕዋሳት ጤንነትን በመጠበቅ በድባቴ፣ በፓርኪንሰንና በአልዛይመር የመጠቃት አደጋን የመቀነስ ዕድል አለው፡፡
ፆም የተፈጥሮ የበሽታ የመከለከል አቅማችንን ይጨምራል፡- ፆም በተለይ የነጭ ደም ሕዋሳትን በአዲስ እንዲተኩ በማድረግ የተፈጥሮ የበሽታ መከላካያችንን በማጠናከር በቀላሉ በበሽታ እንዳንጠቃ ጋሻ ሆኖ ይከላከላል፡፡
#ፆም ቆዳችንን እንዲታደስና በብጉር እንዳንጠቃ ይረዳል፡-
መረዛማ ነገሮች በመወገዳቸውና ኩላሊትና ጉበት ተግባራቸውን ከምን ጊዜውም በተሻለ በመስራታቸው በቆዳችን ላይ አወንታዊ ተፅኖ እንዲኖረው ያደርጋል፡፡
#ፆም በደም ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን በመቀነስ በስኳር ሕመም ምክንያት የሚከሰትን የኩላሊት ውደምት ይቀንሳል፡፡
ፆም ካንሰርን ለመከላከላል ይረዳል፡-
ፆም የዕጢ ወይም ዕባጮችን ዕድገት በመግታት ካንሰር በሰውነታች በሙሉ እንዳይዛመት ይረዳል፡፡
ፆም ለልብ ጤና ወሳኝ ነው፡-
ፆም አይነት ሁለት በተባለውን የስኳር ሕመም እንዳንጠቃ የሚያግዝ በመሆኑ ከልብ ጋር ተያያዥ የሆኑ የጤና እክሎችንም የመቅረፍ ብቃት አለው፡፡