1. ቤት ይቆዩ፦ብዙ COVID-19 ያለባቸው ሰዎች ቀለል ያለ ሕመም ስላላቸው ያለ ህክምና በቤት ውስጥ ማገገም ይችላሉ።
ከስራ ፣ከትምህርት ቤት እና ሌሎች የህዝብ ቦታዎች ቀርተው ለህክምና እርዳታ ካልሆነ በቀር ከቤትዎ ይቆዩ።
•በቤትዎ እረፍት ያድርጉ ፣ፈሳሽ በደንብ ይውሰዱ
•የህክምና እርዳታ ካስፈለገዎ የህዝብ መጓጓዣ አይጠቀሙ ለሚመለከተው የህክምና ተቋም ይደውሉ።
2.እራስዎን በቤትዎ ውስጥ ካሉ ሌሎች ሰዎች እና የቤት እንስሳት ይለዩ።
•በተቻለዎት መጠን በአንድ የተወሰነ ክፍል ውስጥ ይሁኑ እና በቤትዎ ውስጥ ካሉ ሌሎች ሰዎችና የቤት እንስሳት ርቀው መቆየት አለብዎት።እንዲሁም፣የሚችሉ ከሆነ የተለ የመታጠቢያ ቤት እና መፀዳጃ መጠቀም አለብዎት።
•በቤት ውስጥም ሆነ ከቤት ውጭ ካሉ ሰዎች ወይም እንስሳት ጋር መሆን ካስፈለገዎ ከጨርቅ የተሰራ የፊት መሸፈኛ ያድርጉ።
3.የበሽታ ምልክቶችዎን ይከታተሉ።የተለመዱ የኮቪድ-19 ምልክቶች ትኩሳት እና ሳልን ያካትታሉ። የመተንፈስ ችግር ይበልጥ ከባድ ምልክትነው፣ይህም ማለት የሕክምና እርዳታ ማግኘት አለብዎት ማለት ነው።
የኮቪድ -19 ድንገተኛ ማስጠንቀቂያ ምልክቶች ከታዩብዎት ወዲያውኑ የሕክምና እርዳታ ያግኙ።
•የመተንፈስ ችግር
•በደረት ላይ የማያቋርጥ ህመም
•ከዚህ በፊት ያልታየ ግራ መጋባት ወይም •ከእንቅልፍ መንቃት አለመቻል
የፊት ወይም የከንፈሮች መገርጣት እና ሌሎች ለርስዎ የከበደዎት ምልክት ካሉ ሀኪም ጋ ደውለው ያናግሩ።
4.ሐኪምዎን ከመጎብኘትዎ በፊት አስቀድመው ይደውሉ።
•ለመደበኛ ክትትል የሚደረጉ ብዙ የሕክምና ጉብኝቶች በስልክ ወይም በቴሌሜዲስን በመጠቀም ይደረጋሉ ወይም ለሌላ ጊዜ ይተላለፋሉ።
•ለሌላ ጊዜ ሊተላለፍ የማይችል የሕክምና ቀጠሮ ካለዎት ፣ ወደ ሃኪምዎ ቢሮ ይደውሉ።
•ይህ ቢሮው የራሱን ሰራተኞች እና ሌሎች ህመምተኞችን እንዲጠብቅ ያግዛል።
5.ከታመሙ፣አፍንጫዎ እና አፍዎን የሚሸፍን ከጨርቅ የተሰራ የፊትመሸፈኛ ያድርጉ።
•የቤት እንስሳትን ጨምሮ ከሌሎች ሰዎች ወይም እንስሳት ጋር መሆን ካለብዎት (በቤትው ስጥም ጭምር) አፍንጫ እና አፍዎን የሚሸፍን የጨርቅ የፊት መሸፈኛ መልበስ አለብዎት።
•ብቻዎን ከሆኑ የጨርቅ የፊት መሸፈኛውን መልበስ አያስፈልግዎትም።
የጨርቅ የፊት መሸፈኛ መልበስ ካልቻሉ (ለምሳሌ በመተንፈስ ችግር ምክንያት) ሳልዎን እና ማስነጠስዎን በሌላ መንገድ ይሸፍኑ።
•ከሌሎች ሰዎች ቢያንስ 6 ጫማ ያህል ርቀው ለመቆየት ይሞክሩ።
ይህ በአካባቢዎ ያሉትን ሰዎች ለመጠበቅ ይረዳል።
•በኮቪድ -19 ወረርሽኝ ጊዜ የህክምና ደረጃ ያላቸው የፊት መሸፈኛ ጭንብሎች ለጤና እንክብካቤ ሰራተኞች እና ለአንዳንድ የመጀመሪያ ምላሽ ሰጭዎች የተያዙ ናቸው።
•ስካርፍ ወይም የሻሽ/መሃረብ ጨርቆችን ተጠቅመው የጨርቅ የፊት መሸፈኛ መስራት ያስፈልግዎትይሆናል
6.በሚያስሉበት እናበ ሚያስነጥሱበት ወቅት አፍ እና አፍንጫዎን ይሸፍኑ።
በሚያስሉበት ወይም በሚያስነጥሱበት ጊዜአፍዎን እና አፍንጫዎን በሶፍት ይሸፍኑ።
•ጥቅም ላይ የዋሉ ሶፍቶችን ውስጡ ከረጢት ባለው የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ውስጥይጣሉ።
•እጅን ቢያንስ ለ20 ሴኮንዶች ያህል በሳሙና እና በውሃ ወዲያውኑ ይታጠቡ።
•ውሀ እና ሳሙና የሌለ ከሆነ፣እጅዎን ቢያንስ በውስጡ 60% አልኮል በያዘ ባለአልኮል የእጅ ማጽጃ (ብክለት መከላከያ) ያጽዱ።
7.እጆችዎን አዘውትረው ያጽዱ።
እጆችዎን ቢያንስ ለ20 ሴኮንዶች ያህል በሳሙና እና በውሃ አዘውትረው ይታጠቡ።
በተለይ አፍንጫዎን ከነኩ ፣ ካሳልዎት ወይም ካስነጠሱና ፤ መጸዳጃ ቤት ከተጠቀሙ በኋላ፤ እንዲሁም ምግብ ከመብላትዎ ወይም ከማዘጋጀትዎ በፊት አስፈላጊ ነው።
•ሳሙና እና ውሃ ከሌለ ፣የእጅ ማፅጃ ፈሳሽ ይጠቀሙ። ቢያንስ 60% አልኮል ውስጡ ባለው ማጽጃ ሁሉንም የእጆችዎን ክፍሎች በማርጠብ እስከ ሚደርቁ ድረስ እርስ በርስ እያሻሹያድርቁ።
•በተለይም እጆችዎ በሚታይ ሁኔታ የቆሸሹ ከሆነ፣ሳሙና እና ውሃ በጣም የተሻለው አማራጭ ነው።
•ባልታጠበ እጅ ዓይኖችዎን ፣አፍንጫዎን እና አፍዎን ከመንካት ይቆጠቡ።
8.የግል መገልገያ የቤት እቃዎችን ከመጋራት ይቆጠቡ።
•የምግብ ሰሀኖች፣ የመጠጥ ብርጭቆዎች፣ ኩባያዎች፣የመመገቢያ ዕቃዎች፣ፎጣዎች ወይም የአልጋ ልብሶችን በቤትዎ ውስጥ ካሉ ሌሎች ሰዎች አይጋሩ።
•እነዚህን እቃዎች ከተጠቀሙ በኋላ በሳሙና እና በውሃ በደንብ ይጠቧቸው ወይም በእቃ ማጠቢያ ማሽን ውስጥ ያስገቧቸው።
9.እጅ የሚበዛባቸውን” ቦታዎችን በየቀኑ ያጽዱ።
•በክፍል ውስጥ ፣ መታጠቢያ ቤት ያሉ እጅ የሚበዛባቸውን ቦታዎች ያጽዱ እና ከብክለት ነፃ ያድርጉ።
•ሌላ ሰው በጋራ መገልገያ ስፍራዎች ላይ ያሉ ቦታዎችን እንዲያፀዳ እና ከብክለት ነፃ እንዲያደርግ ያድርጉ፣ነገር ግን የመኝታ ክፍልዎን እና የመታጠቢያ ቤትዎን መሆን የለበትም።
•እንክብካቤ የሚያደር ግሰው ወይም ሌላ ሰው የታመመን ሰው መኝ ታቤት ወይም መታጠቢያ ቤት ማፅዳትና ከብክለት ነፃ ማድረግ ተንከባካቢው/ሌላኛው ሰው የፊት መሸፈኛ ጭንብል ማድረግ እና የታመመው ሰው የመታጠቢያ ቤቱን ከተጠቀመ በኋላ በተቻለ መጠን መጠበቅ አለባቸው።
•እንዲሁም በላያቸው ላይ ደም፣ ሰገራ ወይም የሰውነት ፈሳሽ ሊኖርባቸው የሚችሉ አካባቢዎችን ያፅዱና ከብክለት ነፃ ያድርጉ።
10.የቤት ማጽጃዎችን እና ከብክለት ነፃ ማድረጊያዎችን ይጠቀሙ።ቆሻሻ ከሆነ አካባቢውን ወይም እቃውን በሳሙና እና በውሃ ወይም በሌላ ማጽጃ ፈሳሽ ያፅዱ።
ከዚያ የቤት ውስጥ ከብክለት ነፃ ማድረጊያን ይጠቀሙ።
ምርቱን ደህንነቱ በተጠበቀ እና ውጤታማ በሆነ መልኩ መጠቀምን ለማረጋገጥ በመለያው ላይ ያሉትን መመሪያዎች መከተልዎን ያረጋግጡ።
ጀርሞች መሞታቸውን ለማረጋገጥ ብዙ ምርቶች ወለሉ እርጥብ እንደሆነ ለብዙ ደቂቃዎች ማቆየትን ይመክራሉ።
ብዙዎች ጓንት እንደመልበስ እና ምርቱን በሚጠቀሙበትጊዜ ጥሩ የአየር ዝውውር መኖሩን ማረጋገጥ ያሉ ጥንቃቄዎችን ማድረግ ይመክራሉ።
11.በቤት ውስጥ ተለይቶ መቆየትን እንዴትማ ቋረጥ እንደሚቻል
በቤት ውስጥ የቆዩ የኮቪድ-19 ያለባቸው ሰዎች (በቤት ውስጥ ተለይተው የቆዩ) በሚቀጥሉት ሁኔታዎች ውስጥ በቤት ውስጥ ተለይቶ መቆየትን ማቆም ይችላሉ።
1.በሽታን እንደማየያስተላልፉ ለማወቅ ምርመራ ማድረግ የማይችሉ ከሆነ እነዚህ ሶስት ነገሮች ከተሟሉ በኋላ ከቤት መውጣትይችላሉ፡
•ቢያንስ ለ72 ሰዓታት ትኩሳት አልነበርዎትም (ይህ ማለት ትኩሳትን የሚቀንሱ መድሃኒቶች ሳይጠቀሙ ለሶስት ሙሉ ቀናት ትኩሳትየለዎትም) እና
•ሌሎች ምልክቶች መሻሻል አሳይተዋል (ለምሳሌ፣ያለብዎት ሳል ወይም የትንፋሽ እጥረት ሲሻሻል) እና
•የሕመም ምልክቶችዎ መጀምሪያ ከታዩቢ ያንስ 10 ቀናት አልፈዋል።
2.በሽታውን እንደማያስተላልፉ ለማወቅ ምርመራ ማድረግ የሚችሉ ከሆነ እነዚህ ሶስት ነገሮች ከተሟሉ በኋላ ከቤት መውጣት ይችላሉ፡
•ከእንግዲህ ወዲህ ትኩሳት የለዎትም (ትኩሳትን የሚቀንስ መድሃኒት ሳይጠቀሙ)፤
•ሌሎች ምልክቶች መሻሻል አሳይተዋል (ለምሳሌ፣ያለብዎት ሳልወይምየትንፋሽእጥረትሲሻሻል) እና
•በተከታታይ በ24 ሰዓት ልዩነት ሁለት ኔጌቲቭ የምርመራ ውጤቶችን ተቀብለዋል።