በእርግዝና ወቅት እና ከወሊድ በኋላ፣ በሰውነት ውስጥ በሚመረቱ ሆርሞኖች እና ከርግዝና ጋር ተያይዘው በሚመጡ ስነ-ልቦናዊ እና ማህበራዊ ጫናዎች ምክንያት የተለያዩ ስነ-ልቦናዊ እና አእምሯዊ ችግሮች የመከሰት እድላቸው ከፍ ይላል።
ድህረ ወሊድ ድብርት post partum blue ...depression
70%-80% የሚሆኑ እናቶች ልጅ በወለዱ በ1-3 ቀናቸው ውስጥ በትንሹ የመከፋት (postpartum blue) ይኖራቸዋል። ይህም የሚገለጸው :-
1 ድንገተኛ የስሜት ለውጥ ..mood swings
2 ያለምክንያት ማልቀስ
3 ትግስት ማጣት እና ያለምክንያት ማኩረፍ
4 እንቅልፍ ማጣት
5 ጭንቀት እና የብቸኝነት ስሜት
6 የተጠቂነት ስሜት feeling of vulnerability
ከላይ የተጠቀሱትን ምልክቶች መረዳት እና የቤተሰብ እንክብካቤ ምልክቶቹ 10_14 ቀን ውስጥ እንዲጠፋ ይረዳል። ከ ሁለት ሳምንት በላይ የሚቆዩ ምልክቶች ካሉ ሀኪምዎን ማማከር ያስፈልጋል።
ከነዚህ ችግሮች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል:
1. ከወሊድ በኋላ/ድህረ-ወሊድ የሚከሰት ድባቴ[የዛሬ ርዕሳችን]
2. ድህረ-ወሊድ የሚከሰት ከባድ የአንጎል መታወክ
ድህረ-ወሊድ የሚከሰት ድባቴ:
ከወሊድ በኋላ ባሉት 12 ወራት ውስጥ የሚከሰት ድባቴ ሲሆን 10% የሚሆኑ እርጉዝ ሴቶችን ያጠቃል።
ወሊድን ተከትሎ የሚመጣ መጠነኛ የሆነ እና ላጭር ጊዜ ብቻ የሚቆይ ድብርት፣ መነጫነጭ፣ማልቀስ፣እንቅልፍ ማጣት……ብዙ እናቶች ላይ የሚከሰት ሲሆን ህክምና እንደሚያስፈልገው ችግር የሚታየው ግን የድባቴ ደረጃ ላይ ሲደርስ ብቻ ነው (ስለድባቴ ከዚህ በፊት የተጻፈውን ፖስት ይንብቡ)።
ይህ ችግር በእናት ልጅ መካከል የሚኖር ቁርኝት ላይ፣ የህጽኑን እድገት ላይ፣ ትዳር ላይ እንዲሁም የትዳር አጋር የአእምሮ ጤና ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ሊኖረው ይችላል፤ ከዚህ በተጨማሪም ይህ ችግር፣ ከእርግዝና እና ከወሊድ ጋር በተያያዘ እና ባልተያያዘ ድባቴ የመጠቃት እድልን ይጨምራል።
የእናቲቱን ተጋላጭነት የሚጨምሩ ሁኔታዎች:
• ትዳር ውስጥ የሚኖር አለመስማማት
• የኑሮ ጫና
• ከትዳር አጋር ኣኮኖሚያዊ እና ስነ-ልቦናዊ ድጋፍ አለማግኘት
• ያልታቀደ እርግዝና
• ቤተሰብ ውስጥወይም እናቲቱ ላይ የአእምሮ ህመም ከዚህ በፊት ተከስቶ የሚያቅ ከሆነ
• የጽንስ መጨናገፍ
• ጤናማ ልጅ አለመውለድ……
ክትትል እና ህክምና:
በእርግዝና ክትትል ወቅት የእናቲቱን የአእምሮ ጤና ሁኔታ ማጤን በጣም አስፈላጊ ነው
የህመሙ ጥንካሬ ቀልቅል ወይም መካከለኛ ከሆነ ስነ-ልቦናዊ እና ማህበራዊ ህክምና በቂ ይሆናል ተብሎ ይታሰባል።ይሁን እና ህመሙ የከፋ ከሆነ የግዴታ የመድሃኒት ህክምና ሊያስፈልግ ይችላል፤ከመድሃኒት ጋር አብሮ ስነ-ልቦናዊ እና ማህበራዊ ህክምና መስጠትም ይመከራል።
ይሁን እና መድሃኒት በሚታዘዝበት ወቅት መድሃኒቱ ከጡት ማጥባት ጋር ያለውን ግንኑነት ማጤን ያስፈልጋል
ከዚህ ቀደም ድህረ-ወሊድ የሚከሰት ድባቴ የነበራት እናት ወሊድን ተከትሎ መጠነኛ የሆኑ የድባቴ ምልክቶች ከታዩባት በቶሎ ህክምና መጀመር ተመራጭነት አለው።