ባጭሩ ፎረፎር ማለት የራስ ቅል ቆዳን የሚያጠቃ ፈንገስ ነው። መገለጫውም የራስ ቅል ቆዳን በመፈርፈር የማሳከክ ስሜት መፍጠር ነው።
ይህ አይነት ችግር በብዙ ሰዎች ላይ የሚከሰትና በጣም የተለመደ ሲሆን ሰዎችን የሚያሳፍርና ለማከም አስቸጋሪ የሆነ በሽታ ነው።
• ትክክለኛ ምክናየቱ አይታወቅም። በፎረፎር የመያዝ እድልን የሚጨምሩና ጎልቶ እንድታይ የሚያደርጉ ነገሮች ግን አሉ። እነሱም ንፅህናን አለመጠበቅ(አለመታጠብ፡ አለማበጠር): የራስ ቅል ቆዳ ድርቀትን አለመከላከልና የተፈጥሮ የራስ ቅል ቆዳ ቅባትን ታጥቦ አለማስወገድ ፎረፎር ጎልቶ እንድታይ ያደርጋሉ።
• በሽታ የመከላከል አቅምን የሚቀንሱ ህመሞች፡ ምንነታቸው ያልታወቀ የፀጉር ቅባቶችን መጠቀምና የኑሮ አለመመቸትም ለፎረፎር ጎልቶ መታየት ትልቁን ድርሻ ይይዛሉ።
### ፎረፎርን ለማጥፋትና በማይታይ ደረጃ ለማድረስ የሚከተሉትን ያድርጉ።
1. ጭንቀትንና ውጥረትን ያስወግድ።
2. ፀጉረወትን ጧት ጧት ሁል ጊዜ ይታጠቡ።
3. የማይታወቅ ቅባት አይጠቀሙ።
4. የተፈጥሮ የራስ ቅል ቆዳ ቅባትን ታጥበው ይቀንሱ።
5. የራስ ቅል ቆዳ ድርቀትን ይከላከሉ።
6. እራስዎትን(ፀጉረዎትን) ለትንሽ ደቂቃ(3-5 ደቂቃ) ከረር ላለ የፀሀይ ጨረር አጋልጡት።
7. ቲ ትሪ ዘይት (tea tree oil) ይቀቡ።
8. እንዳጠቃላይ እራስዎትን ይጠብቁ። የተመቻቸ ኑሮ ፎረፎርን በእጅጉ ያጠፋልና።
###የሚታዘዙ መድሀኒቶችም አሉና የጤና ባለሙያ ያማክሩ።
ከእነዚህም ውስጥ በሻምፖ መልኩ የሚታዘዙ አሉ። የ ዳንድሩፍ /ፎረፎር/ ሻምፖወች በያዙት አዳኝ ንጥረ ነገር አማካኝነት በ 5 ይከፈላሉ
1. Pyrithione zinc shampoos (DermaZinc, Head & Shoulders, Jason Dandruff Relief 2 in 1). እነዚህ ባክትሪያውንም ፈንገሱንም የሚያጠፋ zinc pyrithione የያዙ ናቸው
2. Tar-based shampoos (Neutrogena T/Gel).
ይሄ ሻምፖ ቀላ ያለ ለስላሳ ስስ ፀጉር ላላቸው የሚመከር ሲሆን ደማቅ ጥቁር ፀጉር ላላቸው የፀጉራቸውን ከለር ሊቀይረው ይችላል
3. Shampoos containing salicylic acid (Neutrogena T/Sal, Baker's P & S, others). ይሄ ፎረፎሩን እስከወዳኛው ለማጥፋት የሚረዳ ነው።
4. Selenium sulfide shampoos (Head & Shoulders Intensive, Selsun Blue, others).
ይሄ ፈንገስ ብቻ ላለባቸው ሰወች የሚታዘዝ ፀረ ፈንገስ ሻምፖ ነው።
5. Ketoconazole shampoos (Nizoral A-D). ይሄ በጭንቅላት ቆዳ ላይ የተከማቸውን የፎረፎር አምጭ ህዋስ ለማስወገድ የሚታዘዝ ነው
ዶር ሰናይት አውራር