የአራስ ህፃናትን ገላ አስተጣጠብ በተመለከተ የተለመዱ ከቤተሰብ የሚጠየቁ ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው
እምብርት ሳይወድቅ ገላ መታጠብ ይችላል?
> አዲስ የተወለዱ ጨቅላ ሕፃን የመጀመሪያውን ገላ መታጠብ መቼ ነው ማግኘት ያለበት /ያለባት ?
.
> ህፃናት አንዴ ቤት ከገቡ በኋላ ምን ያህል ጊዜ መታጠብ ይፈልጋሉ በቀን ሁለቴ ?በቀን አንዴ? በሳምንት ሦስቴ ?
> እምብርት ሳይወድቅ እና ከወደቀ በኃላ ያለው የገላ እጥበት ይለያይ ይሆን?
.
>የአራስ ህፃናት ገላ ስናጥብ ሊወሰዱ የሚገቡ የደህንነት ምክሮች ምንድናቸው?
>የጨቅላ ህፃናት ገላ እጥበት ከመጀመርዎ በፊት የሚያስፈልጉ አቅርቦቶች ምንድናቸው?
.
>የጨቅላ ሕፃናት በ1 ኢንች ብቻ የውሃ ጥልቀት በሰከንዶች ሽርፍራፊ የመስመጥ አደጋ ሊገጥማቸው እንደሚችሉ ያውቃሉን?
.
የአራስ ልጅን ለመጀመሪያ ጊዜ የሰውነት እጥበት ማከናወን ለቤተሰብ ደስታ የሚሰጥ ቢሆንም በተለይ ለመጀመሪያ ወላጅ የራሱ የሆነ ጭንቀት ሊፈጥርም ይችላል። ከዚህም አልፎ በውሃ የመታፈን አደጋም ሊያስከትል ይችላሉ!
ከተወለደ በስንተኛው ቀን ማጠብ አለብኝ እንዴት አድርጌ ወዘተ የተለመደ የእናት ጥያቄዎች ናቸው።
.
- አዲስ የተወለደ ጨቅላ ህፃን ለመጀመሪያ ጊዜ ገላውን መታጠብ ያለበት ምች ነው?
.
በአሁኑ ሰአት የአለም ጤና ድርጅት ጨቅላ ህፃናት ከተወለደ ከ24 ሰአት በኃላ ገላቸውን እንዲታጠብ ይመክራል። እስከ 24 ሰአት ማዘግየት የተፈለገበትም ምክንያት
.
1. ወዲያው ማጠብ የሰውነት ሙቀታቸውን ዝቅ ሊያደርግ ስለሚችል (hypothermia ) እንዲሁም የደም ስኳር መጠናቸውን ሊቀንስ ስለሚችል (hypoglycemia ) አጋላጭነት ስለሚኖረው
.
2. የህፃኑን እና የእናትን ትስስር ለመጨመር ሲባል እና የጡት ማጥባት ስኬትን ሲለሚጨምር
.
3. ህፃናት ከመወለዳቸው በፊት ቆዳቸው ቨርኒክስ በሚባል ነጭ ንጥረ ነገር የተሸፈነ ሲሆን ይህም ተፈጥሯዊ እርጥበት ከማገልገሉም በላይ የፀረ ባክቴሪያ ባህሪ አለው። እንደ አሜሪካ የሕፃናት ህክምና አካዳሚ ይህን ንጥር ነገር ለተወሰነ ጊዜ የራስ ቆዳቸው ላይ መተው እንደሚቻል ይናገራሉ።
.
- አምብርታቸው ያልወደቁ ጨቅላ ህፃናት እንዴት ነው ገላቸውን መታጠብ ያለባቸው?
.
ህፃናት ገና እንደተወሰዱ ህትብታቸው በራሱ ደርቆ ድኖ ተቆርጦ እስኪወድቅ ድረስ ገላቸውን ማጠብ አይቻልም። ስለዚህ ለሰስ ባለ ውሃ ውስጥ በርከት ያለ ንፁ ጥቅልል ጥጥ በመንከር በጥጡ መፅዳት ይቻላል።
.
እትብታቸው ደርቆ ድኖ የወደቀ ጨቅላ ህፃናት ገላ ማጠብ ከመጀመርዎ በፊት ሊያዘጋጇቸው የሚያስፈልጉ ግብአቶች
- ለህፃናት ማጠቢያነት የተዘጋጀ የማጠቢያ ፕላስቲክ
- የህፃናት የተዘጋጀ ቫዝሊን እና ሳሙና
.
- ከታጠበ በኃላ የሚቀይረው ሙሉ ልብስ እና ማቀፊያ
- ንፋስ እና ቅዝቃዜ የሌለው የማጠቢያ ክፍል
.
- በቂ ሞቅ ያለ ውሃና ለመበረዣ የሚሆን ቀዝቃዛ ውሃ በተለያየ እቃ ማቅረብ
- እጃችሁን በሳሙና መታጠብ
.
- ህፃኑን በማጠብያ እቃ ውስጥ በቂ ቀዝቃዛ እና ሙቅ ውሃ ይበርዙ
- ውሃው ሲበረዝ እጅግ ጥንቃቄ ማድረግ አለብን። የነሱ ቆዳ እጅግ ለስላሳ ስለሆነ ለቃጠሎ ሊጋለጡ ይችላሉ።ይህንን የቃጠሎ አደጋ ለመቀነስ ሁል ጊዜ ከተበረዘ በኃላ በክርናችን መለካት አለብን።
.
- ስናጥባቸው ተሙለጭልጨው ሊወድቁ ስለሚችሉ ማጠቢያውን እና አካባቢውን አስተካክሎ መጀመር
- የህፃኑን ልብስ ካወለቁ በኃላ ሳያቆዩት እንደማጠቢያው አመችነት ህፃኑን እቀፉት። በሚያቅፉበት ጊዜ አንገቱን እራሱን አማካኝ በማድረግ በግራ እጅ በመያዝ በቀኝ እጃችሁ ለህፃኑ ማጠቢያ ተብሎ በተዘጋጀው ዕቃ ላይ ቀስ ብላችሁ እና ቀና አድርጋችሁ በቂጥ አስቀምጡ።
.
ልብ ሊባል የሚገባው እንዳያፍነው ውሃ ወደ ፊቱ እንዳይመጣ እና ወደ አይኑ አፍንጫው እንዳይገባ በመጠንቀቅ እጃችሁን ትንሽ ሳሙና ቀብታችሁ ፀጉሩን ከግንባሩ ወደ ኃላ እጠቡት። የህፃናት ገላ ማጠቢያ ሳሙና አይን ስለማያቃጥል ሳናበዛ በጣታችን ነካ እያደረግን ቀስ አድርጎ ማሸት። እጃችሁን ውሃ ወስጥ እየነከራችሁም ፊቱን እጠቡት።
.
ልብ ሊባል የሚገባው ፊት ላይ ውሃ መፍሰስ የለበትም ሊያፍናቸው ስለሚችል ጆሮን የጆሮን ስር አንገት አጥባችሁ ስጨርሱ ወደ ታች ተሙለጭልጮ እንዳይወድቅ ይዘው ይጠቡ።
.
ሁሉም የሰውነት ክፍል በጥንቃቄ ጥርት ብሎ ከታጠበ በኃላ ለማለቅለቂያ ባዘጋጃችሁት ለብ ያለ ውሃ አለቅልቃችሁ አፅዱት ቀጥሎም ወዲያውኑ ተዘርግቶ በተቀመጠው ፎጣ ላይ አስተኞቶ ጥቅልል በማድረግ ገላው ላይ ያለውን ውሃ አድርቁ። ቀጥሎም የቆዳ ድርቀት ለመከላከል ካቀረባችሁት ቅባት ገላውን ይቀቡ። በመፀዳጃ አከባቢ በርከት አድርገው ይቀቡ። በመጨረሻም ሙሉ ልብሱን አልብሳችሁ በማቀፊያ በመጠቅለል እቅፍ ያድርጉት።
.
የህፃናትን የቆዳ ድርቀት ለመከላከል ሲባል በሳምንት ሶስት ጊዜ ማጠብ በቂ ነው ።
.
መልካም ጤንነት ተመኘሁ
ለብዙሃን እንዲደርስ ሼር በማድረግ ይተባበሩን ?❤️
- ዶ/ር መሐመድ በሽር ፤