Rabies በተለምዶ "የእብድ ውሻ በሽታ"

እኔ በአንድ ወቅት በምሰራበት ክፍል ውስጥ አንድ 11 አመት ታዳጊ "በእብድ ውሻ" ተነክሶ ቤተሰብ ችላ በማለት እና ክትባቱን በቶሎ ባለመውሰዱ ለህልፈት ተዳረጓል።እስቲ ስለ rabies በተለምዶ "የእብድ ውሻ በሽታ" ትነሽ ነገር ልበላቹ።

የሬቢስ በሽታ ምንድን ነው?
 
-በተለምዶ የእብድ ውሻ በሽታ(Rabies) የምንለው ሬቢስ በሚባል ቫይረስ አማካኝነት የሚመጣ ከእንስሳት ወደ የሰዉ ልጅ የሚተላለፍ በሽታ ነው።
-የእብድ ውሻ በሽታ የተባለበት ምክንያት በአበዛኛው የቫይረሱ ተሸካሚዎች በአካባቢያችን የሚገኙ ውሾች በመሆናቸው ነው።ከዚህ በተጨማሪ የለሊት ወፍ፣ፈረስ፣ላም፣ የቫይረሱ ተሸካሚ ሊሆኑ ይችላሉ።
-ከዉሻ ጋር ተያይዞ የሚመጣ የሬቢስ በሽታ በአብዛኛው ታዳጊ ሀገራትን የሚያጠቃ ሲሆን በተለይ ህጻናት ለጆችን ስለበሽታው እና ከትባቱ በቂ ግንዛቤ በሌላቸው የሀገራችን ክፍሎች ላይ በብዛት ይስተዋላል።
 
መተላለፊያ መንገዶች ምንድን ናቸው?
 
-በቫይረሱ ከተጠቁ እንስሳት በተለይ ከውሾች ወደ የሰው ልጅ በንክሻ ወይም በመቧጨር ከአፉቸው በሚወጣ ፈሳሽ(saliva) በቀጥታ ቆዳን ዘልቆ የሚገባ ከሆነ ወይም በሰወነታችን ትኩስ ቁስል(fresh skin wounds) ካለ ሊተላለፍ ይችላል።
-በተለይ የተነከስነው ወይም የተቧጨርነው አንገት እነ ከአንገት በላይ ከሆነ ቫየረሱ በፍጥነት ወደ ማእከላዊ የነርቭ ስርአት(central nervous system) ቅርብ ስለሆነ በፍጥነት ወደ አንጎል(brain) በመድረስ ለሞት ሊዳርገን ይችላል።
-የሬቢስ በሽታ theroetically ከቫይረሱ ተሸካሚ ሰው ወደ ሰው በንክሻ ይተላለፋል ተብሎ ይታሰባል።
 
ምልክቶቹስ ምንድን ናቸው?
 
-አንድ ሰው በቫይረሱ ከተጋለጠ በዃላ ምልክት እስከሚያሳይ( incubation period) ከ3ሳምንት እስከ 3ወር ሊቆይ ይችላል።
-ምልክት የሚያሳዩ ሰዎች የተነከሰበት ቦታ ለይ መጠዝጠዝ አና መደንዘዝ፣ትኩሳት፣እራስ ምታት፣ማቅለሽለሽ፣ማስመለስ፣ጡንቻ አካባቢ የህመም ስሜት፣ ፍራቻ፣ከመጠን በላይ ምራቅ መኖር፣ለመዋጥ መቸገር፣ቅዠት፣ግራ መጋባት፣ዉሃን መፍራት(hydrophobia)፣እንቅልፍ ማጣት፣ የከፉ ደረጃ ሲደርስም ለኮማ ከዛም ለሞት ሊዳረግ ይችላል።
-ምልክቶቹን ማሳየት የጀመረ ሰው የመዳን አድሉ እጅግ በጣም ጠባብ ነው።
 
እንዴት መከላከል አነችላለን?
 
-የቤትም ሆነ የዱር እንስሳ ካለን ማስከተብ
-ሌላው መርሳት የሌለብን ነገር ክትባቱን ባልተከተቡ እንስሳት ከተነክሰን ወይም ጥርጣሬ እንኳን ቢኖርብን ግዜ ሳንሰጥ ወዲያውኑ የህክምና ባለሙያ በማማከር የተጋላጭነት ክትባቱን(post exposure prohpylaxis) መዉሰድ አለብን።
ህክምናውስ?
-የሬቢስ በሽታ ይሄ ነው ሚባል ህክምና የለውም።ምክነያቱም የሬቢስ ቫይረስ ሰውታችን ውስጥ ከገባ እራሱን ስለሚደብቅ በጸረ ቫይረስ(Anti viral) አንኳን መዳን አይችልም።
-ስለዚህ ማንኛውም አይነት ቁስል በሰውነታችን ለይ ካለ በአግባቡ መታከም እና ተጋላጭ ከሆንን ጊዜ ሳነሰጥ የህክምና ቦታ በመሄድ ከትባቱን መከተብ ብቸኛ አማራጮች ናቸው።
-በአጠቃላይ የሬቢስ በሽታ ችላ የማይባል ለህልፈት የሚዳርግ በሽታ ነው።
 
ጤና ይብዛሎ
Dr.Ermias Mamo