የአፍሪካ የማስክ ሳምንት

የአፍሪካ የማስክ ሳምንት (#AfricaMaskWeek) በሀገራችን እንዲሁም በመላው አፍሪካ

ከሕዳር 14 እስከ ሕዳር 21 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ይካሄዳል፡፡  ይህ 'ማስክ አፍሪካ' በሚል መሪ ቃል የተጀመረው ንቅናቄ ማስክን በአግባቡ ማድረግ የሚኖረውን ጠቀሜታ ለማስተማር እና በአግባቡ ለመጠቀም የሚያግዝ  ነው ፡፡
 የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በበርካታ ሀገራት  ጉዳቱ እየጨመረ እና በሕብረተሰብ ጤና እንዲሁም ማህበራዊ ሁነቶች ላይ ጫና በሚያሳድርበት በአሁኑ ሰዓት ኮቪድ-19ኝን ለመከላከል በዓለም ጤና ድርጅት የተረጋገጠ አንደኛው መንገድ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ በአግባቡ ማድረግ በመሆኑ ማህበረሰቡ በንቅናቄው ትክክለኛ የማስክ አጠቃቀምን በመማር እና የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ በትክክል በማድረግ እና ሌሎችም እንዲያደርጉ በማገዝ የበሽታውን ስርጭት እንግታ፤ኃላፊነታችንን እንወጣ !
#COVID19Ethiopia
#AfricaMaskWeek