በብዙ ሴቶች ላይ የሚታይ ችግር ነው
ብዙ ጊዜ በታዳጊ ወጣቶች ላይ (የወር አበባ በጀመረ 4-5 ዓመት ዉስጥ) የሚታይ ሲሆን እድሜ እየጨመረ ሲሄድ ይቀንሳል
?, በ 2 ይከፈላል
Primary (አንደኛ)
?, በማህፀን የዉስጥ ግድግዳ የሚመረቱ prostaglandin የተባሉ ኬሚካሎች ሲለቀቁ የማህፀን ጡንቻ መኮማተር በማምጣት ህመም እና ወደ ማህፀን የሚሄደው ደም እንዲቀንስ ሲያደርጉ ነው
Secondary (ሁለተኛ)
?, የወር አበባ እንዳይፈስ በሚያግዱ ነገሮች (ኢንፌክሽኖች, የመራቢያ አካላት አከባቢ የሚከሰት እጤ, endometriosis (ማህፀን የዉስጥ ክፍል ዉስጥ መገኘት ያለባቸው ሴሎች ከማህፀን ዉጪ ሲያድጉ
?, የወር አበባ የጀመረ ጊዜ ወይም በጥቂት አመታት ዉስጥ የሚጀምር ህመም ብዙ ጊዜ የመጀመሪያ ጎራ ዉስጥ የሚመደብ ሲሆን ሁለተኛው አመታት ካለፈ በሁአላ ይከሰታል
?, ምልክቶች
?, በታችኛው የሆድ ክፍል አከባቢ ቁርጠት, አንዳንዴ ወደ ጀርባ እና ታፋ ላይም ሊሰማ ይችላል
?, ህመሙ ትንሽ ሰዓት ቀደም ብሎ ወይም የወር አበባ እንደጀመረ ተከስቶ ከ 48-72 ሰዓት ሊቆይ ይችላል
?, ምን መደረግ አለበት?
?, ከጤና ባለሙያ እንደ አስፈላጊነቱ ሙሉ የሆድ እና የማህፀን ምርመራ ይደረጋል
?, መድሀኒቶች, NSAID የተባሉ ጎራ የተመደቡ መድሀኒቶች, ወሊድ መቆጣጠሪያ እንክብል ወዘተ ሀኪም ባዘዘው መሰረት መወሰድ አለበት
?, ሙቀት
ዉሃ አፍልቶ (40°c) ለማስቀመጫ የተዘጋጁ ላስትኮች (heat pads) ወይም በዉሃ መጠጫ ላስትክ በጨርቅ ጠቅልሎ የታችኛው የሆድ ክፍል ጋር ማድረግ (ብዙ መሞቅ የለበትም)
?, አመጋገብ (በቫይታሚኖች የበለፀገ ምግብ ማዘውተር)
?, እንቅስቃሴ በብዛት ማድረግ ይገባል
ጤና ይስጥልን