የኬሚካል አደጋዎች የሚከሰቱት ሆነ ተብሎ ወይም በአደጋ ምክንያት አደገኛ ኬሚካሎች ወደ አየር ሲለቀቁ፣ በምግብ እና ውሃ ውስጥ ሲጨመሩ ነው።
ኬሚካሎቹ የሚተኑ፣ ፈሳሽ ወይም ጠጣር ሊሆኑ ይችላሉ። ኬሚካሎቹ ለሰው ልጆች እና ለከባባዊ ንብረት አደጋ ሊሆኑ ይችላሉ። ሰዎች ኬሚካሎችን ከአየር ጋር ተቀላቅሎ ወደ ሰውነታቸው ከገባ፣ ከቆዳ ጋር ከተገናኘ ወይም ወደ ሰውነት ከገባ ጉዳት ሊያከትሉ ይችላሉ።
የሚከተሉትን የኬሚካል አደጋ ምልክቶችን ያስተውሉ።
ውሃ የቋጠሩ ዓይኖች
- የመተንፈስ ችግር ወይም በኃይል ትንፋሽ ሲያጥር
- መንቀሳቀስ ወይም መራመድ ሲያቅት
- ግራ የመጋባት ስሜት
- ድንገተኛ የሆኑ መንገዳገድ
- ቆዳ ማቃጠል
የሚሞቱ ወይም የሚታመሙ ወፎች፣ አሳዎች ወይም ትናንሽ እንስሳቶች መብዛት ሌላው የኬሚካል አደጋዎች ምልክቶች ሊሆኑ ይችላሉ።
የኬሚካል አደጋዎች በሚከሰቱበት ወቅት
በቴሌቪዥን፣ በሬዲዮ በማህበራዊ ሚዲያዎች እና በኢንተርኔትየሚሰጡ መግለጫዎችን ያድምጡ።
- የአከባቢው እና የግዛቱ ባለስልጣናት ምን አይነት ምልክቶችን ማስተዋል እንደሚኖርባችሁ ይነግሯችኋል።
- ባለስልጣናት በቤትዎ መቆየት ካለብዎ ወይም ከቤት መውጣት ካለብዎ አና የት መሄድ እንደሚኖርብዎ ያሳውቃሉ።
- በቤት ውስጥ እንዲቀመጡ ከተነገረዎ፡ ማሞቂያዎችን፣ ኤሲዎችን እና ፋኖችን ያጥፉ።
- ንፋስ ማስገቢያዎችን ይዝጉ።
- ሁሉኑም መስኮቶች እና በሮች ይዝጉ።
ህመም ከተሰማዎ፣ በፍጥነት ሃኪሞ ጋር ይደውሉ ወይም ወደ ሆስፒታል ይሂዱ።
ኬሚካል ሲለቀቅ ከተመለከቱ፡
- አከባቢውን በፍጥነት ለቀው ይሂዱ።
- ለመተንፈስ በሚያሰችሎት መልኩ አፍ እና አፍንጫዎን በጨርቅ ሸፍነው አየር እያጣሩ ይተንፍስ።
- መጠለያ ይፈልጉ። ኬሚካሉ በህንጻ ላይ ከሆነ በኬሚካሉ መካከል ሳያቋርጡ ህንጻውን ጥለው ይውጡ። ከህንጻው መውጣት የማይችሉ ከሆነ፤ በተቻለዎ መጠን ከኬሚካል ይራቁ።
- ከህንጻው ውጪ ከሆኑ በተቻለዎ መጠን ከህንጻው ርቀው ይሂዱ። የንፋስ አቅጣጫን መለየት ከቻሉ፤ ንፋሱ ወደሚነፍስበት ተቃራኒ አቅጣጫ ይጓዙ። ውጪ ላይ መቆየት ካልቻሉ ወይም ከኬሚካሉ መራቅ ካልቻሉ፤ ቤት ውስጥ ይግቡ።
- ስለ ኬሚካል አደጋዎች ካላወቁ ፖሊስ ጋር ይደውሉ።
ለኬሚካሉ እንደተጋለጡ ካወቁ ወይም ለኬሚካሉ ሳልጋለጥ አልቀርም ካሉ፡
- ለብስዎን ያውልቁ እና ላስቲክ ውስጥ ያስቀምጡት። ላስቲኩን በደንብ አድርገው ይቋጥሩት።
- ገላዎትን ይታጠቡ ወይም ቆዳዎትን እና ጸጉርዎን በውሃ እና በሳሙና ይታጠቡ። ኬሚካሉን ቆዳዎ ላይአይከኩ። ወጪ ላይ ከሆኑ ውሃ የሚያገኙበትን አማራጭ ይፈልጉ።
- ነጹህ ልብስ ይቀይሩ።
- የኬሚካል አደጋ ምልክቶችን ካለብዎ የህክምና እርዳታ ይጠይቁ።
ኬሚካል በትክክል ሰዎች ላይ ከተኘ፤ ባለስልጣናት ለኬሚካል የተጋለጡ ሰዎችን ከብክለት ነጻ ለማድግ በሂደት ውስጥ ሊያሳልፏቸው ይችላሉ። ይህም ኬሚካሉ ከሰውነታቸው ላይ ለማስለቀቅ ልብሳቸውን እንዲያወልቁ እና ገላቸውን እንዲታጠቡ ማድረግ ሊሆን ይችላል። ይህ ተንቀሳቃሽ ገላ መታጠቢያ በመጠቀም ሊሆን ይችላል።