ካንሰር በሴሎች ውስጥ ማደግ የሚጀምር ህመም ነው። ሰውነታችን ብዙ ሚሊዮን በሚሆኑ ሴሎች የተሰራ ነው።
እነዚህ ሴሎች ተሰብስበው በጋራ ደግሞ ስጋ (tissue) ብልቶች/የሰውነት ክፍሎች (organ) ለምሳሌ ጡንቻ እና አጥንት፣ ሳምባ እና ኩላሊትን የመሳሰሉትን ይፈጥራሉ። በእያንዳንዱ ሴል ውስጥ የሚገኝ ጂን ደግሞ ሴሎችን እንዲያድጉ፤ እንዲሰሩ፤ እንዲባዙና እንዲሞቱ ያዛል። የተለመደው ሁኔታ ሴሎቻችን በጂኖቻችን ይታዘዛሉ እና እኛም ጤናማ ሆነው እንኖራለን።
ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ ከአንዳንድ ሴሎች የሚመነጨው ትእዛዝ ሴሎችን ባልተለመደ ሁኔታ እንዲሰሩ ያደርጋቸዋል። ይህም ከተለመደው ውጪ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል። እነዚህ የተናጉ ሴሎች ያድጋሉ እናም ቁጥጥር በሌለው መንገድ ይራባሉ። ከጥቂት ጊዜ በሗላ በአንድ ላይ የተሰበሰቡ/በቡድን ያሉ የተናጉ ሴሎች እብጠትን ወይንም ዕጢን ይፈጥራሉ።
እብጠቶች/ዕጢዎች ጤናማ (ካንሰር የሌለባቸው)ወይንም ታማሚ (ካንሰር ያለባቸው) ሊሆኑ ይችላሉ። ጤናማ ዕጢዎች አንድ ቦታ ብቻ ነው የሚሆኑት እና ህይወትን አደጋ ላይ ሊጥሉ የሚችሉ አይደሉም።
ታማሚ የሆኑት (ካንሰር ያለባቸው) ዕጢዎች አካባቢያቸው ያለውን አካል (tissue) ማጥቃት እና ወደ ሌሎች የሰውነት ክፍሎችም መራባት ይችላሉ። ወደ ሌላ የሰውነት አካል መራባት የሚችሉት የካንሰር ሴሎች ሜታስታስስ (metastases) ተብለው ይጠራሉ።
ካንስር ያለው ዕጢ በሰውነት ውስጥ ለመሰራጨቱ (metastasized-ሜታስታሳይዝድ ለመሆኑ) የመጀመሪያው ምልክት በአካባቢው ያለ የሌላ ዕጢ ዕብጠት ነው። ሆኖም ካንሰር በማንኛውም የሰውነት አካል ሊሰራጭ ይችላል። ስለዚህ ካንሰር ያለበትን ዕጢ/እብጠት በተቻለ ፍጥነት በጊዜ መለየትና ማከም አስፈላጊ ነው።
የካንሰር ስሞች የካንሰር ሴሎቹ ከተገኙበት ብልት/የሰውነት አካል ጋር የተያያዙ ናቸው። ለምሳሌ የጡት ካንሰር፤ ያንጀት ካንሰር፤ የቆዳ ካንሰር ሲሆን ከጡት የጀመረ ነገር ግን ወደ ጉበት የተሰራጨ ካንሰር ከሆነ ደግሞ መጠሪያው የጡት ካንሰር ከታወከ ጉበት ጋር የሚል ነው።
ምን ማድረግ እንደሚገባዎ What you can do
የጡትዎን ጤንነት መጠበቅ ሌላውን የሰውነት አካልዎትን ለመጠበቅ ከሚወስዱዋችው እርምጃዎች ውስጥ አንዱ ነው። ይህንንም በሚከተሉት መንገዶች ማድረግ ይቻላል።
· ለጡት ካንሰር ስለሚያጋልጡ(risks) ነገሮች ማወቅ
· የመጋለጥ ዕድልን ማሳነስ
· ምልክቶችንና(signs) ስሜቶችን(symptoms) ለይቶ ማወቅ
· የሚመከሩትን የጡት ምርመራዎች ማድረግ
· የበለጠ ለማወቅ መሞከር
ለጡት ካንሰር ስለሚያጋልጡ ነገሮች ማወቅ Know the risk factors for breast cancer
አንዳንድ ሴቶች በጡት ካንሰር የመያዝ ዕድላቸው ከፍተኛ ሊሆን ይችላል። የጡት ካንሰርን ያመጣል ተብሎ ተለይቶ የታወቀ ምክንያት የለም ነገር ግን ለበሽታው የመጋለጥ ዕድልን ይጨምራሉ ተብለው የሚታሰቡ ነገሮች አሉ።
· እድሜ፦ የጡት ካንሰር በማንኛውም የእድሜ ክልል ውስጥ ባሉ ሴቶች ላይ ሊታይ ይችላል ነገር ግን በእድሜ በገፉ ቁጥር በበሽታው የመያዝ እድል ይጨምራል።
· በቤተሰብ ውስጥ የጡት ካንሰር ታሪክ ካለ (በተለይ እናት፤ አህት ወይንም ልጅ ከማረጫ እድሜያቸው በፊት የጡት ካንሰር ይዟቸው ከነበረ ወይንም ቢ አር ሲ 1 ወይንም ቢ አር ሲ 2 (BRCA1 BRCA2 genes) የተባሉ ጂንሶች ተገኝተውባቸው ከሆነ
· በቤተሰብ ውስጥ የማህፀን እና ኮሎሬክታል (ያንጀት) ካንሰር ከነበረ
· ቀደም ብሎ በተከሰተ የጡት ህምመ ምርመራ ያልተለመዱ ሴሎች (abnormal cells) ታይተው/ ተገኝተው ከነበረ
· ልጅ ያለመውለድ ወይንም የመጀመሪያ እርግዝና ከ30 አመት በሗላ ሆኖ ከነበረ
· የወር አባባ ከተለመደው አማካይ እድሜ በፊት ጀምሮ ከነበረ ወይንም የማረጫ ጊዜ ከተለመደው አማካይ ዕድሜ በላይ ከተራዘመ ወይንም ሁለቱም ባንድላይ ተከስተው ከሆነ
· ጠንካራ (dense breast tissue) የጡት ይዘት
· የሆርሞን መተኪያ ህክምና/ቴራፒ(hormone replacement therapy) ለ5 አመታት ወይንም ከዚያ በላይ ወስደው ከነበረ
እነዚህ ነገሮች ከሀኪሞ ጋር በመነጋገር በእርስዎ ጤና ላይ ያለውን/ያላቸውን ተጽዕኖ ማወቅ ይገባል
አንድ ተለይቶ የታወቀ የጡት ካንሰር ምንጭ/ምክንያት የለም ነገር ግን አንዳንድ ነገሮች ለበሽታው ያለንን የመጋለጥ እድል የሚጨምሩ ይመስላሉ። እነዚህ ነገሮች በእርስዎ ላይ ቢታዩ ግን የጡት ካንሰር እድገት ጀምሯል ማለት አይደለም። ሆኖም ይህ በጡት ካንሰር የመያዝ እድልዎ ከፍተኛ ሊሆን ይችላል ማለት ነው።
አብዛኞቹ በጡት ካንሰር ህመም የተጠቁ ሴቶች በሽታውን ይፈጥራሉ ተብለው
የሚታሰቡት ምልክቶች አልታዩባቸውም፤ በቀላሉ ሴቶች ከመሆናቸውና በዕድሜ ከመግፋታቸው (በተለይ ከ50 አመት በላይ)በቀር። ከዚህ ሌላ ሌሎች በሽታውን ይፈጥራሉ ተብለው የሚታሰቡት ነገሮች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦
o ቀደም ብሎ በጡት ካንሰር ተይዘው ከነበረ
o በቤተሰብ ውስጥ የጡት ካንሰር ህመም (በተለይ በእናት፤ በእህት፤ ወይንም በልጅ ከማረጫ እድሜ በፊት ታይቶ ከነበረ ወይንም በቤተሰብ የዘር ሀረግ ምክንያት በጂንስ(genes) ለምሳሌ BRCA1 እና BRCA2 ከነበረ።)
o በቤተሰብ ውስጥ የታየ የማህጸን ካንሰር ከነበረ
o መጠኑ ከአማካይ በላይ ለሆነ ኤስትሮጅን ሆርሞን (ሰውነትዎ በተፈጥሮው የሚያመርተውን) በሚከተሉት ምክንያቶች ተጋልጠው ከነበረ።
o ልጅ ያልወለዱ ከነበረ ወይንም የመጀመሪያ ውልጃ ከ30 አመት በፊት ሆኖ ከነበረ
o የወር አበባ በጣም በልጅነት እድሜ ተከስቶ ከነበረ
o የማረጫ ጊዜ አማካይ ከሆነው የማረጫ እድሜ በሗላ ከጀመረ
o የሆርሞን መተኪያ ህክምና/ቴራፒ(ኤስትሮጅን እና ፕሮጀስትሮን) ካምስት አመት በላይ ወስደው ከነበረ
o ጠንካራ የጡት አካል እንዳሎት በማሞግራም ምስል ከተረጋገጠ
o ከጡት በሚወሰድ የናሙና ምርመራ ምክንያት የታየ የጡት ለውጥ ለምሳሌ በቁጥር የጨመረ ያልተለመዱ ሴሎች ከታዩ/ከተገኙ ምንም እንኳን የካንሰር ሴሎች ባይሆኑም (atypical hyperplasia)
o በደረት አካባቢ የተደረገ የራዲየሽን ህክምና (ለምሳሌ ከ30 አመት እድሜ በፊት ሆድኪን ሊይምፎማ (Hodgkin lymphoma) ለማከም ተጠቅመው ከሆነ) አንዳንድ ነገሮች በጡት ካንሰር የመያዝ እድልዎን ይጨምራሉ። ለበሽታው በሚከተሉት ምክንያቶች የበለጠ የተጋለጡ ሊሆኑ ይችላሉ።
o ከመጠን በላይ ወፍራም መሆን(በተለይ ደግሞ ከማረጫ እድሜ በሗላ)
o አልኮል መጠጥ የሚጠጡ ከሆነ
o የወሊድ መቆጣጠሪያ ክኒን የሚጠቀሙ ከሆነ
ሌሎች ተጨማሪ ለጡት ካንሰር ስለሚያጋልጡ ሁኔታዎችና ጉዳዩች ጥናቶች መረደጋቸውን ቀጥለዋል። ለምሳሌ የመጋለጥ እድልዎ እንዴት ካመጋገብዎ እና ከሰውነት እንቅስቃሴ ልምድዎ ጋር ግንኙነት እንዳለው እየተጠና ነው። በተጨማሪ ሲጋራ ማጨስ በተለይ ደግሞ ሁለተኛ አጫሽ መሆን (ከሚያጨሱ ሰዎች ጋር በመሆን የሚወሰድ የሲጋራ ጪስ) እና ለአንዳንድ ኬሚካሎች መጋለጥ ለምሳሌ ፒሲቢ (polychlorinated biphenyis) የመሳሰሉትም በመጠናት ላይ ናቸው።