በኢትዮጵያ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ቁጥር መቶ ሺህ (100,000) አለፈ

የኮቪድ-19  ወረርሽኝ በሽታ በሃገራችን በምርመራ ከተገኘበት ከመጋቢት 4 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን ለ1,534,470 ሰዎች የላብራቶሪ ምርመራ

ተደርጎላቸው 100,327 ሰዎች ቫይረሱ የተገኘባቸው ሲሆን የ1537 ወገኖቻችንን ህይወት አጥተናል፡፡  አሁን ላይ 286 ሰዎች በጽኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ ይገኛሉ፡፡
እነዚህ ቁጥሮች ሰዎች ናቸው!!
እያንዳንዱን የሕመምና የሞት ክስተት ለብዙዎች ጭንቀት፣ ሀዘን፣ ቁጭት እና ውጣ ውረድ ምክንያት መሆኑን ስናስብ ይሕ ከቁጥር በላይ ነው፡፡
በመሆኑም እያንዳንዱ ግለሰብ፤ ቤተሰብ፤ ሁሉም መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፤ የሐይማኖት ተቋማት፣ ሲቪክ ማህበራት፤  አገልግሎት ሰጪ ተቋማት፤ ጤና ባለሙያዎች፤  መምህራንና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ለመከላከከልና  ለመቆጣጠር ተግባር ላይ በባለቤትነት እና በኃላፊነት ስሜት አጠናክረው እንዲሠሩ እናሳስባለን፡፡  
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
ዛሬም እንጠንቀቅ !!
#COVID19Ethiopia