Hiking በረጅም መንገድ ብዙ ጊዜ ከከተማ ዉጭህ የሚደረግ የእግር ጉዞ ነው
?, አንዲ አይነት የእግር መንገድ ለጤናችን በጣም ጥሩ ነው, አካላዊም ሆነ ስነልቦናዊ ጤናን ለመጠበቅ ይረዳል
?, ከብዙ የጤና ጥቅሞች ዉስጥ በጥቂቱ
?, የልብ በሽታ የመያዝ እድላችንን ይቀንሳል አንዲሁም የደም ግፊት አንዲቀንስ ይረዳል
?, የአጥንት ጥንካሬ እንዲጨምር ያረጋል
?, ጡንቻዎቻችን በተለይም የመቀመጫ, የእግር እና ታፋ አከባቢ የሚገኙ ጡንቻዎችን እንዲጠነክሩ ያደርጋል
?, የተቃና እና የተስተካከለ አረማመድ እንዲኖር ያደርጋል
?, ክብደት እንድንቀንስ በማረግ ክብደት ከመጨመር ጋ ተያይዘው የሚመጡ እንደ ስኳር የኮሌስትሮል መጨመር የመሳሰሉትን ለመከላከል ይረዳል
?, ከጭንቀት እና ከድብርት ለመላቀቅ በጣም ጠቃሚ ነው
?, ለረጅም የእግር ጉዞ የሚረዱ ነገሮች
?, ቀስ ብሎ መጀመር, ለጀማሪ ሰው አጠር ካለ መንገድ ጀምሮ ቀስ በቀስ ወደ ከፍ ያሉ ተራራማ መንገዶች መሄድ ይቻላል
?, መደገፊያ በትር መያዝ
?, ከፍታ መንገዶችን መዉጣት በተለይ ስብን ለማቃጠል ይጠቅማል
?, ወጣ ገባ መንገድ የተቃና አረማመድን ለመጠበቅ ይረዳል
?, ክብደት ያለው ነገር በጀርባ መያዝ የጀርባ ጡንቻዎች እንዲንቀሳቀሱ ይረዳሉ, ዉሃ ቢሆን ይመረጣል
?, ይህንን የእግር ጉዞ ልምድ አርጎ በየጊዜዉ እንቅስቃሴ ማድረግ
ጤና ይስጥልን