በስራ ገበታ ሳለን ቀላል የማይባሉ እናቶች አዉቀውም ሆነ ሳያውቁ "የጡቴ ወተት በቂ ስላልሆነ የላም ወተት ተጨማሪ ጀምሬለታለው" ብለው ሳያበቁ ቱከት ተቅማጥ
ታመው ማየት የተለመደ ነገር ነው ።
.
ልጆች የላም ወተት መች ነዉ መጀመር ያለባቸው? ጤናማ የሆነ የልጅ አመጋገብ ምንድነው?
.
ህፃናት የተስተካከለ አካላዊና አዕምሮዊ እድገት እንዲኖራቸዉ ጤናማ የአመጋገብ ዘዴ ጉልህ ድርሻ አለዉ፡፡ ይህ ጤናማ የሆነ የአመጋገብ ዘዴ ልጆቹን ከተለያዩ በሽታዎች እንደ ተቅማጥ ፣ የሳምባ ምች ፣ የጀሮ ምርቀዛ ('ኢንፌክሽን') እና ሌሎችንም ተላላፊ በሽታዎች በመከላከል ከፍተኛ የሆነ አስተዋፅኦ አለዉ፡፡ .
ጤናማ የአመጋገብ ዘዴ የምንላቸዉ ምንድናቸው?
.
- የመጀመሪያዎቹ 6 ወራት ዕድሜ በዚህ የዕድሜ ክልል ዉስጥ ህፃናት ያለምንም ተጨማሪ ምግብ የእናት ጡት ብቻ በቀን ከ8-12 ጊዜ እንዲወስዱ ይመከራል፡፡ጨቅላ ህፃናት ወዲያዉ በተወለዱ በ30 ደቂቃ ዉስጥ የእናት ጡት መጀመር አለባቸዉ፡፡
.
በተለምዶ በተለይ በገጠራማዉ አካባቢ እንዲሁም በከተማዎች አልፎ አለፎ ጨቅላ ህፃናት ወዲያዉ እንተወለዱ ከእናት ጡት በፊት የሚሰጡ (prelactal feeding) እንደ አብሽ ፣ ቅቤ ፣ ሻይ ፣ ዉሃ በስኳር የመሳሰሉትን
መስጠት ለኢንፌክሽን ስለሚያጋልጣቸዉ ጎጂ ባህላዊ ልማድ ነዉ፡፡
.
- ከስድስት እስከ አስራ ሁለት ወራት ዕድሜ
.
በዚህ የዕድሜ ክልል ዉስጥ ህፃናት ከየእናት ጡት በተጨማሪ ተጨማሪ ምግብ መጀመር አለባቸዉ፡፡
.
እድሜያቸዉ ከ 6-8 ወር ለሆኑ ህፃናት ተጨማሪ ምግቦችን በፈሳሽ መልክ (እንደ አጥሚት) በቀን ከ2-3 ጊዜ እንዲሁም ከ8- 12 ወር ለሆናቸዉ በከፊል ጠጣር መልክ (እንደ ገንፎ) በቀን 4-5 ጊዜ መመግብ ያስፈልጋል፡፡
.
በዚህ የዕድሜ ክልል ዉስጥ ጡት ማጥባት የሚቀጥል ሲሆን ነገር ግን የእናት ጡት ወተት መጠን እየቀነሰ የሚሄድበት ጊዜ ስለሆነ ለህፃናት የሚሰጠዉ ተጨማሪ ምግብ በዓይነትም በመጠንም በደንብ መጨመር አለበት፡፡ ተጨማሪ ምግቦችን በጠጣር መልክ (እንደ እንጀራ፣ ዳቦ፤ እንቁላል፣ ሥጋ፣ ወዘተ የቤተሰብ ምግቦችን) መጀመር ይቻላል፡፡
.
- ከስድስት ወር ቀደመው ሌላ ነገር ቢጀምሩ ምን የጤና ችግር ይገጥማቸዋል?
ልጆች ብዙ ወይም በቂ የእናት ጡት እንዳያገኙ ያደርጋቸዋል::
ልጆች ለተቅማጥ በሽታ
እንዲጋለጡ ያደርጋቸዋል::
.
- ተጨማሪ ምግብ ከስድስት ወር አልፈው ቢጀምሩ እሳ?
ልጆች የሚያስፈልጋቸውን ተጨማሪ ሀይልና ንጥረ ምግቦች እንዳያገኙ ያደርጋል፡፡
ልጆች ለመቀጨጭና ለተለያዩ የማእድን እጥረት ሊጋለጡ ይችላሉ፡፡
.
ልጆች የላም ወተት መች ነዉ መጀመር ያለባቸው?
.
- ህጻናትን ቶሎ የላም ወተት ማስጀመር ያለው የጤና ጉዳት የአለም ጤና ዲርጅትና የተለያዩ ጥናቶች እንደሚያሳዩት የተለየ አስገዳጅ ሁኔታ ካልተፈጠረ በስተቀር የላም ወተት ከአንድ አመት በፊት መሰጠት የለበትም፡፡ ከአንድ አመት በፊት የላም ወተት የሚወስዱ ህፃናት በተለይም መጠኑ ከ20 ounce ወይም ግማሽ ሊትር በላይ ከሆነ የአንጀት መድማትና አይረን የተባለዉን ንጥረ ነገር ከአንጀት ወደ ደም እንዳይመጠጥ በማድረግ በአይረን እጥረት ምክንያት የሚከሰት የደም ማነስ (Iron deficiency anemia) ያመጣል፡፡
.
- የላም ወተት ለልጆች በቶሎ ማስጀመር የጤና ጉዳቶች
o ዝቅተኛ የአይረን መጠን ስላለው ለደም ማነስ ችግር ያጋልጣል
o ከፍተኛ የፕሮቲን ይዘት ስላለው
ለአንደኛው የስኳር ህመም ያጋልጣቸዋል
o የህጻናት ሆድ ድርቀት
o የወተት አለርጂ
o ላክቶዝ ንጥረነገር በሰውነት ውስጥ አለመኖር በወተት ውስጥ ለሚገኘው የላክቶዝ ንጥረነገር መብላላት አለመቻል ያጋልጣቸዋል፡፡
o ተቅማጥ የመሳሰሉትን የጤና እክሎች ያመጡባቸዋል
.
አንብበው ሲጨርሱ ለወዳጅ ዘመድዎ ሼር ያድርጉት መልካሙን ሁሉ ተመኘው
ዶ/ር መሐመድ በሽር የህፃናት ሐኪም