ኢንፍሉዌንዛ(ወረርሽኝ) ልጅህ በወረርሽኙ በሚጠቃበት ወቅት
ስለበሽታው ለህፃናት መንገር፡፡
- ልጅ/ህ ወረርሽኙን ለመቋቋም ሊያደርገው በሚችለው ነገርና ወረርሽኙን ወደ ሌሎች እንዳያዛመት ማድረጉ ላይ ማተኮር አለብህ፤
- ልጅ/ህ የእንፍሉዌን ዛክትባት እንዲሰጠው አድርግ፡፡ መርፌ ሲወጋ ሊጠዘጥዘው ይችላል ይሁን እንጂ በኋላ ከመታመም ይታደገዋል፡፡ በአፍንጫ የሚነፋ የወረርሽኝ መከላከያም ለማግኘት ይቻላል፡፡
- ልጆች ወደ ታመሙ ሰዎች እንዳይጠጉ አድርግ
- በታመሙበት ወቅት በሶፍት ወይም በጨርቅ ላይ እንዲያስሉ ወይም እንዲያስነጥሱ አበረታታቸው፡፡ የተጠቀሙበትን ጨርቅ ወይም ሶፍት ወደ ቆሻሻ ማጠራቀሚያ ወርውር፡፡ ሶፍት ለጊዜው ማግኘት ባይችሉ አፋቸውንና አፍንጫቸውን በእጃቸው መሸፈን አለባቸው፡
- እጆቻቸውን ደጋግመው በሳሙናና ሞቅ ባለ ውሀ ከ15 እስከ 2ዐ ሰኮንዶች ድረስ እንዲታጠቡ አበረታታቸው፡፡ በዚህ ረገድ አንተው ራስህ በመታጠብ አርአያ ሁናቸው፡፡
- በታመሙበት ወቅት ወደ ስራ ወይም ወደ ትምህርት ቤት እንዳይሄዱ አበረታታቸው፡፡ ህመሙ እስኪ ለቃቸው ድረስ ከሰዎች እርቀው እንዲገኙ እርዳቻው፡፡
- ጤናማ ልምዶችን አበረታታ፡፡ ጤናማ ምግቦችን መውሰድ፣ በቂ እንቅልፍና የአካል እንቅስቃሴ ማድረግ፡፡
- የሚያቀርቧቸውን ጥያቄዎች በመመርኮዝ በሽታውን እንዴት እንደሚከላከሉትና ወረርሽኙና ሌሎች ተውሳኮች እንዳያስፋፉ ምከራቸው፡፡