Asthma (አስም)

አስም ማለት በራሱ ጊዜ ወይም በጊዜአዊ ህክምና ሊስተካከል የሚችል የአየር ትቦ መዘጋት ነው::

  • አስም ያለባቸው ሰዎች አስም ከሌለባቸው በበለጠ ሳንባቸው በባእድ ነገሮች የመቆጣት እድል አለው::
  • ይህ በሽታ በአለም እስከ 300000 ድረስ ሰዎችን ያጠቃል:: ?, አስም በየትኛውም የእድሜ ክልል የሚከሰት ሲሆን በልጅነት 2 አጥፍ ወንዶች ከሴቶች በላይ ይጠቃሉ እድሜ ሲጨምር ግን እኩል ይሆናል::
  • ብዙ ጊዜ አስም ያለባቸው በቆዳ እና በመተንፈሻ አካል ላይ በሚታዩ አለርጂዎች ይጠቃሉ::

 

  • ለአስም የሚያግልጡ ነገሮች
  • በቤተሰብ
  • የአየር ቧንቧ ቶሎ መቆጣት
  • ቫይረሶች
  • ከልክ ያለፈ ውፍረት
  • የስራ አይነት (ፋብሪካ ውስጥ)
  • ሲጋራ
  • የሳንባ ኢንፌክሽን
  • አየር መበከል

 

  • በሽታው እንዲነሳ አስተዋፆ የሚያረጉ
  • ሽታ
  • ቫይረስ
  • ከባድ እንቅስቃሴ
  • ብርድ
  • መድሀኒቶች
  • ጭንቀት
  • አቧራ, እንስሳት እና የመሳሰሉት

 

  • ምልክቶች በአብዛሃኛው ሚታዩት
  • ሳል
  • ደረት ላይ ስር ስር የሚል ድምፅ
  • ደረት መጨምደድ
  • ትንፊሽ ማጠር ሲሆኑ ብዙ ጊዜ ማታ ማታ የመነሳት ባህሪይ አለው::
  • በተጨማሪም ለማውጣት የሚያስቸግር የሚዘገለግ አክታ ሊኖር ይችላል::

 

  • ይህ በሽታ የሚታወቀው በታካሚው ላይ በሚታየው ምልክቶች ሲሆን በተጨማሪም spirometry በተባለ መሳሪያ እንጠቀማለን::

 

  • ምን መደረግ አለበት
  • ወደ ሆስፒታል በመሄድ አስፈላጊ ከሆነ ወይም የ ኦክሲጅን መጠን ከ <90% ከሆነ ኦክሲጅን አንዲሰጥ ይደረጋል::
  • በተጨማሪም አንደደረጃው ታይቶ በሀኪም የሚሰጥ መድድሀኒትን በአግባቡ መውሰድ ያስፈልጋል::