በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ መመርመሪያ ኪት ከአንድ ወር በኋላ ማምረት እንደሚጀመር የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል!

የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ ከአንድ ወር በኋላ ከቻይና መንግሥት ጋር በመተባበር የመመርመሪያ ኪት ለማምረት ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።

ለዚህም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ድጋፉን ከምታደርገው የቻይና መንግሥት ጋር በጉዳዩ ላይ እየመከሩ መሆኑን ገልጸዋል።

“የመመርመሪያ ኪቱን በአገር ውስጥ ማምረት ሲጀመር ከውጭ የሚገባውን ኪት ሙሉ በሙሉ ያስቀራል” ያሉት ዶክተር ደረጀ፣ ምርቱ ለሌሎች የአፍሪካ አገራት እንደሚዳረስም ተናግረዋል።

ከእዚህ በተጨማሪ በየጊዜው እያደገ የመጣውን የመመርመር አቅም በእጅጉ ከፍ እንደሚያደርገው ጠቁመዋል።

Via ENA