የአደጋ ጊዜ ቅደመ ዝግጅት

አደጋ ማለት አውሎ ንፋስ የቀላቀለ ዝናብ፣ የቤት ቃጠሎ፣ ጎርፍ ወይም የቦምብ ጥቃት ሊሆን ይችላል። ቀድመውን በማቀድ እራስዎን እና የቤተሰብ አባላትዎ ላይ የአደጋ ጊዜው ሊያስከትል የሚችለውን ጉዳት ይቀንሱ።

ለመዘጋጀት እንዲረዳዎ እነዚህን ሶስት ቅደመ ተከተሎች ይከተሉ፡

1. ያቅዱ ለእራስዎ እና ለቤተሰብዎ።
2. ለአደጋ ጊዜ የሚረዱ ቁሶችን ቀድመው ያዘጋጁ በመኖሪያ ቤቶች፣ በሥራ እና በመኪናዎ ውስጥ።
3. በአደጋ ጊዜ ምን ማድረግ እንዳለብዎ እና የት መሄድ አንደሚኖርብዎ ለማወቅ መረጃዎችን ያዳምጡ። 

ደረጃ 1። ያቅዱ
ለእራስዎ እና ለቤተሰብዎ የአደጋ ጊዜ ማምለጫ መንገድ ያቅዱ። ስለእቅዱ ቤተሰብዎን ያማክሩ። የቤተሰብዎ አባላት በቤት ውስጥ መቆየት ወይም የተሻለ ደህንነት ወዳለበት ሥፍራ ሊሄዱ ይችላሉ። የቤተሰብ አባላትዎ እርስ በእርስ እንዴት ሊገናኙ እንደሚችሉ ይወስኑ። አንድ የቤተሰብ አባል ሁሉንም የቤተሰቡን አባል በስልክ ወይም በኢ-ሜይል እንዲያገኙ መውሰን ይችላሉ። እርሶ ከሚኖሩበት ከተማ ውጪ ያለ ሰው በአደጋ ጊዜ ለማግኘት መሞከር የተሻለ አማራጭ ሊሆን ይችላል ምክንያቱም በተመሳሳይ ከተማ ውስጥ ያሉ ሰዎች በተመሳሳይ ችግር ውስጥ ሊሆኑ ይችላሉ ስልክም ላይሰራ ይችላል። ቤተሰቡ የት እንደሚገናኝ እና ሁሉም የቤተሰብ አባላት እንዴት እዛ እንደሚገናኙ ያቅዱ።

እቅድዎ ማካተት ካለበት መካከል፡

  • የአደጋ ጊዜ ተጠሪ የሚሆነ ሰው ስልክ እና የኢ-ሜይል አድራሽ። ይህን መረጃ ለቤተሰብ አባላት፣ የሥራ ባልደረቦች፣ በትምህርት እና የህጻናት እንክብካቤ ማዕከላት ጋር ያጋሩ።
  • እርስዎ ቢታመሙ ወይም በመኖሪያ ቤት መገኘት ካልቻሉ ለልጆችዎ አስፈላጊውን እንክብካቤ ሊያደርግ የሚችል ሰው ይለዩ።
  • በአከባቢው እና ከከተማ ውጪ የሚገኙ የአደጋ ጊዜ ተጠሪ ሰዎችን አድራሻ ይመዝግቡ።
  • የእያንዳንዱ የቤተሰብ አባል የጤና መረጃ፣ ይህም የትውልድ ቀን፣ የደም አይነት፣ አለርጂ፣ አሁን ያለ እና ያለፈ ህመም፣ አሁን እየወሰዱ ያሉት መድሃኒት ካለ ከሚወሰደው መጠን ጋር ይጠቀሱ፣ የህክምና መሳሪያ እና የጤና መድህን ካርድ ፎቶኮፒ።
  • የሃኪሞን ስም እና ስልክ ቁጥሮች።
  • በሥራ ቦታ፣ በትምህርት ቤት እና በመኖሪያ ቤት አቅራቢያ የሚገኙ ሆስፒታሎችን ስልክ ይመዝግቡ።
  • የግዘቱ እና የአከባቢው የጤና ዲፓርትመንት አድራሻ እና ስልክ ቁጥር።
  • የሃኪሞን ስም እና ስልክ ቁጥሮች።
  • ሃይማኖታዊ እና መንፈሳዊ መረጃዎች።
  • ቢታመሙ እና በመኖሪያ ቤትዎ መገኘት የማይችሉ ከሆነ የቤት እንስሳዎችን መንከባከብ የሚችል ሰው ይለዩ። የቤት እስሳዎችን በየወቅቱ ያስከትቡ እንዲሁም እንስሳቱ ወደ መጠለያ መሄድ ካለባቸው የክትባት ሰርተፊኬታቸውን ኮፒ ያስቀምጡ።
  • የቤት እንስሳ ሃኪም ስም እና ስልክ ቁጥሮች።

ለልዩ አጋጣሚዎች ቀድመው ያቅዱ

በህጻናት እንክብካቤ ማዕከላት እና በትምህርት ቤት ውስጥ ያሉ ህጻናት – አብዛኛዎቹ ትምህርት ቤቶች እና የህጻናት መንከባከቢያ ማዕከላት የአደጋ ጊዜ እቅዶች አሏቸው በተጨማሪም እሳት፣ የመሬት መንቀጥቀጥ ወይም አውሎ ንፋስ የቀላቀለ ዝናብ ቢከስት በሚል ልምምድ ያደርጋሉ። ትምህርት ቤቶች እና የህጻናት መንከባከቢያ ማዕከላት የእርስዎን የሥራ፣ የመኖሪያ፣ ስልክ እና የኢ-ሜይል አድራሻ እንዳላቸው ያረጋግጡ። የሚከተለውን መጠየቅዎን እርግጠኛ ይሁኑ፡

  • በአደጋ ጊዜ ወላጆች እንዴት እንደሚደወልላቸው።
  • ልጆችዎን ከአደጋ ለመጠበቅ መወስድ ያለባቸውን ቅድመ ተከተል።
  • ተጨማሪ ውሃ፣ ምግብ እና የመጀመሪያ እርዳት ቁሶች መኖራቸውን።
  • ትምህርት ቤቶች ለህመም የተጋለጡ ልጆችን ከጤነኞች እንዴት እንደሚለዩ።
  • አከባቢው ተለቅቆ የሚወጣ ከሆነ ልጆች ወደየት እንደሚወሰዱ።

ሥራ – የአደጋ ጊዜ እቅዶች ምን እንደሆኑ እና የሥራ ፖሊሶች ዙሪያ ከቀጣሪዎ ጋር ይወያዩ። ወደ ሥራ መሄድዎ ግድ ከሆነ ለቤተሰብዎ ያቅዱ።

የልዩ ፍላጎት ሰዎች – የሚያስፈልግዎትን የህክምና እርዳት እጅ ላይ በሚታሰር አንባር ያሳዩ ላይ ወይም አንገት ላይ በሚታይ መልኩ ጽፈው ያንጠልጥሉ። በአደጋ ጊዜ ሊረዳ የሚችልዎ ሰው ያዘጋጁ። ይህ ሰው ወደ ቤትዎ መግባት መቻል እና ማድረግ የሚኖርበት ድጋፍ ማወቅ ይኖርበታል።

  • በቤት ውስጥ የሚኖሩ፤ ተጨማሪ መድሃኒቶች እና ግብዓቶችን ያስቀምጡ።
  • የኩላሊት እጥበት ወይም መቋረጥ የማይችል ህክምና የሚከታተሉ ሰዎች ከተለመደው ቦታ በተጨማሪ ሌሎች የአገልግሎት መስጫ ስፍራዎችን ማወቅ ይኖርባቸዋል።
  • በልዩ ፍላጎት መስጫ ተቋማት ውስጥ የሚኖሩ፤ ተቋሙ የአደጋ ጊዜ እቅድ ሊኖራቸው ይገባል።

ደህንነቱ የተጠበቀ መጠለያ – በመርዝ የተበከለ አየር ካለ በቤት ውስጥ እንዲቆዩ ሊነገርዎ ይችላል። ማሞቂያዎችን፣ ኤሲዎችን እና ፋኖችን ያጥፉ። ንፋስ ማስገቢያዎችን ይዝጉ። ሁሉኑም መስኮቶች እና በሮች ይዝጉ። መረጃ እንዲያገኙ ቴሌቪዥን ይመልከቱ ወይም በባትሪ የሚሰሩ ሬዲዮችን ያድምጡ።

የቤት እንስሳትስ፡ ለቤት እንስሳት በቂ የሆነ ምግብ፣ ውሃ፣ መድሃኒት እና ሌሎች አስፈላጊ ቁሶችን ያኑሩ። የቤት እንስሳዎችን ከእርሶ ጋር ይዘው ለመውጣት ይዘጋጁ ካልሆነ ደግሞ ሊንከባከብልዎ የሚችል ሰው ያዘጋጁ። የቤት እንስሳት በወቅቱ ያስከትቡ መረጃዎን አብረው ይያዙ።

ደረጃ 2። የአደጋ ጊዜ ቁስ ያዘጋጁ
አስቸኳይ አደጋ ቢከሰት፣ ምግብ እና ውሃ ለቀናት ወይም ለሳምንታት ላያገኙ ይችላሉ፤ ኤሌክትሪክም ላይሰራ ይችላል። ቤትዎችን መልቀቅ ካለብዎ ለአደጋ ጊዜ የሚሆኖትን ምግብ በእቃ፣ በፕላስቲክ፣ ወይም በሻንጣ አሸገው ያዘጋጁ። የአደጋ ጊዜ የምግብ ክምችትዎን በየወሩ ይቀይሩ።

ለ 3 ቀናት የሚዘልቅ ለእያንዳንዱ ሰው እና የቤት እንስሳ የሚከተሉት ቁሶች ክምችት ይኑሮዎት።

1. ምግብ እና ሌሎች ቁሶች

  • ንጹህ ውሃ፣ የታሸጉ የፕላስተክ እቃ መያዣዎች- ለእያንዳንዱ ሰው እና የቤት እንስሳ አንድ ጋሎን ያስቀምጡ
  • ለምግብነት ወዲያው ሊውሉ የሚችሉ የታሸጉ ስጋዎች፣ ፍራፍሬ እና አትክልቶች
  • የታሸጉ ጣሳዎችን መክፈቻ
  • ፕሮቲን እና የፍራፍሬ ይዘት ያላቸው
  • ሲሪያል፣ ግራኖላ፣ ለውዝ እና ክራከርስ
  • የለውዝ ቅቤ
  • የደረቁ ምግቦች ለምሳሌ የደረቁ አትክልቶች እና እርጥበታቸው የወጣ ምግቦች
  • የታሸጉ ጁሶች
  • የዱቄት ወተት ወይም የታሸጉ ወተቶች
  • የህጻናት ወተት እና የታሸጉ የህጻናት ምግቦች
  • የቤት እንስሳት ምግቦች

2. መሠረታዊ አቅርቦቶች

  • የእጅ ባትሪ እና ተጨማሪ ባትሪ ድንጋይ
  • በባትሪ የሚሰራ ራዲዮ እና ተጨማሪ ባትሪ ድንጋይ
  • ስሊፒንግ ባግ እና ብርድልብስ
  • ለህጻናት ዳይፓር እና መመገቢያ ጡጦ
  • ማጽጃ ሶፍት ወረቀት ብክለት የሚያስወግዱ ማጽጃዎች ወይም በረኪና ያለው ማጽጃ። ካሻዎ እራሰዎ ውሃ እና በርኪና እንድላይ መጠነው መጠቀም ይችላሉ። ሲቀላቅሉ አስር እጅ ውሃ በአንድ እጅ በረኪና ይቀላቅሉ።
  • ሶፍት እና የሽንት ቤት ሶፍት ወረቀቶች……
  • የሴቶች ንጽህና መጠበቂያ
  • ከወረቀት የተዘጋጁ ሳህኖች፣ ለፕላስቲክ የተሰሩ መመገብያዎች እና ሶፍት
  • ውሃ በማያስገባ እቃ የተቀመጠ ክብሪት
  • ፕላስቲክ፣ የተለያየ መጠን ያላቸው ፕላስተር ማጣበቂያዎች
  • ቆሻሻ መጣያ
  • ክዳን ያለቸው ፕላስቲክ መያዣ
  • በሃኪም የታዘዙ መድሃኒቶች
  • የእያንዳንዱን የቤተሰብ አባል የጤና መረጃ የያዘ ውሃ የማያስገባ ፕላስቲክ እኚህ መረጃዎች መታወቂያ፣ የጤና መድህን ሰርተፊኩት እና የልደት ሰርተፊኬትን ይጨምራል።
  • ለጆሮ ማዳመጫ እና ለዊልቼር ተጨማሪ ባትሪዎች

3. የመጀመሪያ እርዳታ ቁስ

  • ዲጂታል ቴርሞሜትር (ሙቀት መለኪያ)
  • የተለያየ መጠን ያላቸው የቁስል መሸፈኛ ፕላስተሮች፣ ባለ ሁለት እና አራት ኢንች መጠን ያላቸው ባደንዴጅ፣ ባለ ሶስት መዓዘን ባንዴጅ እና የሚጠቀለሉ ባንዱጆች።
  • ባንዴጅ
  • የአልኮል ይዘት ያለው እጅ ማጽጃ ይጠቀሙ።
  • ልብሶችን ይጠቡ እና ጊዜያዊ ልብሶች
  • አንቲባዮቲክ የሆኑ ቅባቶች
  • ጓንቶች
  • መቀስ፣ መረፌ፣ መረፌ ቁልፍ እና የመሳሰሉ ኮተን ጥጥ
  • ያለ ዶክተር ትዕዛዝ የሚገዙ መድሃኒተች ትኩሳትን፣ ህመምን፣ የሆድ በሽታን፣ ሳል፣ ጉንፋን እና ተቅማጥን ማከም የሚችሉ መድሃኒቶች

ከመኖሪያ ቤትዎ መውጣት ግድ ከሆነብዎ፣ የሚከተለውን መያዝዎን አይዘንጉ፡

  • ልብስ እና ጠንካራ ጫማዎች
  • ኮት፣ ኮፍያ፣ የዝናብ ልብስ እና ጓንት
  • የጥርስ ሳሙና፣ የጥርስ ብሩሽ እና ሌሎች ተመሳሳይ ቁሶች
  • ቀድመው የተሞሉ ስልክ መደወያ ካርዶች
  • የቤትዎ እና የመኪና ቁልፍ
  • ጥሬ ገንዘብ እና ክሬዲት ካርድ
  • መጽሃፍት፣ መጫወቻ ካርታ እና ሌሎች መጫዎቻዎች

የመኪና መለዋወጫ

አነስተኛ የሆኑ የአደጋ ጊዜ መኪና መለዋወጫዎች ሁሌም በመኪናዎ ውስጥ ያቆዩ፡

  • የእጅ ባትሪ ከተጨማሪ ባትሪ ድንጋይ ጋር
  • ስሊፒን ባግ ወይም ብርድልብስ
  • የመንገድ አቅጣጫ ካርታ
  • የመጀመሪያ እርዳታ ቁስ
  • ጎማ መጠገኛ ቁስ፣ የመኪና ባትሪ ማስነሻ ገመድ

ደረጃ 3 መረጃዎችን ያድምጡ

የአከባቢው እና የግዛቱ ባለስልጣናት ነዋሪዎችን ለመጠበቅ እቅድ አላቸው። ይረጋጉ እና በሬዲዮ እና ሬዲዮ ሪፖርቶችን ያስምጡ ከዚህ በተጨማሪ በማህበራዊ ሚዲያዎች ወይም በኢንተርኔትይከታተሉ። የመብራት አገልግሎት ቢቋረጥ ሬዲዮ እና ተጨማሪ ባትሪ ድንጋይ ያዘጋጁ። ግነኙነት ላይ እክሎች የሚኖሩ ከሆነ፣ ለእርሰዎች እና ለቤተሰብዎ የተሻለውን አማራጭ ያቅዱ።