ቤት ውስጥ ብቻ ስንውል ምን ይመጣል ከገንዘብ ባሻገር?
በኮሮና ምክንያት ቤት ውስጥ ስንቀመጥ ሊከሰቱ የሚችሉ በርካታ ችግሮችም አሉ።
1. የእአምሮ ህመም ድብርት፣ ጭንቀት
2. የደም መርጋት/DVT
3. ከክብደት መጨመር ጋር የሚከሰቱ ህመሞች ስኳር፣ ደም ግፊት ፣ የልብ ህመም ( እድሜያቸው ከ40 በላይ ለሆኑ)
4.የቤተሰብ ግጭት እስከ ትዳር መፍረስ የሚደርስ
ሊከሰቱ ይችላሉ።
#መፍትሄ #
1.በቀን ውስጥ ቢያንስ ለ 30 ደቂቃ አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ ( ቢያነስ መራመድ)
2.በቂ እንቅልፍ መተኛት
3.የአመጋገብ ስርኣትን ማስተካከል ምሳሌ ስኳር እና ጨው መቀነስ፣ አትክልት ፍራፍሬ ማዘውተር
4. ቤት ውስጥ ሆኖ የሚሰራ ስራ መንደፍ
5.አለመረበሽ ፣ አላስፈላጊ የሆኑ ኢንፎርሜሽኖችን መራቅ ፣ ስለበሽታው ከሚመለከተው አካል ብቻ መልክትን መውሰድ
6. የኢንተርኔት አጠቃቀም ላይ እንቅልፍን በማያዛባ ደረጃ መጠቀም ( መገደብ) ።
ዶ/ር ሰኢድ አራጌ
ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል