በወር አበባ ወቅት ሰውነትዎ ፕሮስታግላንዲን የሚባሉ ኬሚካሎችን ያመነጫል።እነዚህ ኬሚካሎች በምጥ ጊዜ የሚኖረው አይነት የማህጸን ቁርጠት ያመጣሉ።
አንዳንድ የማህጸን ህመሞች ለምሳሌ ኢንዶመትርዮሲስ፣ የማህጸን እጢ እና የማህጸን ኢንፌክሽን በወር አበባ ወቅት የሚኖረውን ህመም ያባብሱታል።
የህመሙ አይነት
• የፐሬድ ህመም ያላቸው ሴቶች የታችኛው የሆድ አከባቢ ቁርጠት ይኖራቸዋል። ቁርጠቱ ቀላል ወይም ከባድ ሊሆን ይችላል። በተጨማሪም የጀርባ ወይም በጭን አከባቢ ህመም ሊኖር ይችላል። ህመሙ ፐሬድ እንደጀመረ ወይም ከመጀመሩ ከጥቂት ሰአታት በፊት ሊጀምር ይችላል።
አንዳንድ ሴቶች በተጨማሪ የሚከተሉት የህመም ስሜቶች ይታዬባቸዋል
• ማቅለሽለሽ
• ተቅማጥ
• በጣም ከባድ የድካም ሰሜት
• ራስ ምታት
• ሆድ የመንፋት ስሜት
መከላከል
• የፐሬድ መምጣት ምልክቶች እንደጀመሩ ወዲያውኑ እንደ ዲክሎፌናክ የመሳሰሉ የህመም ማስታገሻ ክኒኖችን መዋጥ ይጀምሩ። ከዚያም 2 ወይም ለ 3 ቀናት መውሰድዎን ይቀጥሉ።
• በታችኛው የሆድዎ አከባቢ ላይ የሞቀ ፓድን ወይም ሙቅ ውሃ የያዘ ጠርሙ ያድርጉ
• በመደበኛነት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ያድርጉ
ከስር የተዘረዘሩት ምልክቶች ከታዩብዎ ሐኪምዎን ወይም ነርስዎን ያማክሩ
• ህመሙ እየባሰ ከመጣ
• ህመሙ የህመም ማስታገሻ መድኃኒት ካላስታገሰው
• ህመሙ ከፐሬድ ውጪ የሚቀጥል ከሆነ
ምርመራዎች
• የርስዎ እድሜ ፣ ሌሎች ተጨማሪ ምልክቶች እና ግለሰባዊ ሁኔታዎች መሰረት በማድረግ ምንአይነት ምርመራ ማድረግ እንዳለብዎት ሐኪምዎ ወይም ነርስ ይወስናሉ።
አብዛኛዎቹ ሴቶች የአካል ምርመራ ብቻ ያስፈልጋቸዋል። አንዳንድ ጊዜ ግን ተጨማሪ ምርመራዎች ሊያስፈልጉ ይችላሉ።
• የማህጸን አልትራሳውንድ
• የአባላዘር በሽታዎች ምርመራ
የወር አበባ ህመም ህክምና
ህክምናው በመንስኤው ላይ የተመሰረተ ነው። በጣም የተለመዱት ሕክምናዎች የሚከተሉትን ያጠቃልላል።
• የህመም ማስታገሻ መድሃኒቶች
• የወሊድ መከላከያ ክኒን ወይም ሌላ ዓይነት የወሊድ መቆጣጠሪያዎችን (ሆርሞኖችን) ያጠቃልላል::