የአቮካዶ የጤና ጥቅም

አንድ አቮካዶ በአማካይ 150 ግራም ሲሆን 240 ካሎሪ ፣ 22 ግራም ፋት ፣ 10 ግራም ፋይበር አለው ።

1. ብዙ ንጥረ ነገሮች የያዘ ሲሆን አንድ አቮካዶ እስከ 850 ሚሊ ግራም ፓታስየም (የሙዝ 2×) የያዘ ሲሆን ፓታስየም ለጉልበት ፣ ለልብ ፣ የደም ስኳር ለማስተካከል ፣ ሰውነት ዘና እንዲል ይረዳል ይህም ጥሩ እንቅልፍ ለመተኛት ፣ የደም ግፊት ለመቀነስ ፣ የሰውነት ቁጣ (inflammation ) ለመቀነስ ይረዳል ።
ከዚህ በተጨማሪ አቮካዶ ፎሌት ፣ ቫይታሚን ሲ ፣ ቫይታሚን ኬ ፣ ቫይታሚን ቢ5 ፣ ቢ6 ፣ ማግኒዚየም ፣ማንጋኒዝ ፣ዚንክ እና ሌሎች ።
2. ከፍተኛ የማይሟሟ ክር (insoluble fiber ) አለው ይህም የተለያዩ ጥሩ የአንጀት ባክቴሪያዎች እንዲኖሩ ይረዳል ። እነዚህ ባክቴሪያዎች ይህን ፋይበር በመጠቀም short chain fatty acid ይሰራሉ ይህም የኢንሱሊን ሆርሞን sensitivity ይጨምራል ይህም የስኳር ህመም ለመከላከል ይረዳል ፣ ልብን ከጉዳት ይጠብቃል ፣ ክብደትን ለመቆጣጠር ይረዳል ፣ በሽታ የመከላከል አቅምን ይጨምራል ።
3. ከፍተኛ ጥሩ ፋት አለው
5. የአይን ጤናን ለመጠበቅ ይረዳሉ ፦ አቮካዶዎች እይታዎን ሊጎዱ የሚችሉ የብርሃን ሞገዶችን የሚወስዱ ሉቲን እና ዘአዛንታይን አላቸው ፡፡
6. ለድብርት ተጋላጭነትን ይቀንሳል
7. የአጥንት መሳሳትን ይከላከላል
8. ለምግብ መፈጨት ይጠቅማል
9. በሰውነት ውስጥ የሚገኙ መርዛማ ንጥረ ነገሮችን ለማስወገድ ይጠቅማል
10. የረጅም ጊዜ በሽታዎችን ለመቀነስ ይረዳል ( የስኳር በሽታ ፣ የደም ግፊት ፣ የልብ ህመም ፣ ካንሰር ፣ አልዛይመር )
#ያጋሩ