የህፃናት የሆድ ቁርጠት

 የህፃናት የሆድ ቁርጠት በተለይም እስከ 4 ወር ዕድሜ ያሉ ህፃናት ላይ የሚታይ ህመም ነው።

ዋነኛ ምልክቶቹም የማያቋርጥ ለቅሶ እና መነጫነጭ ናቸው።
• በአብዛኛው የሚጀምረው ህፃናቱ በተወለዱ 3-6 ሳምንት ዕድሜያቸው ነው።

• የሆድ ቁርጠት ያለባቸው ህፃናት በቀን ከ3 ሰዓት በላይ፣በሳምንት ከ3 ቀን በላይ እና ከ3 ሳምንት ጊዜ የበለጠ ነው።
• ይህ ህመም ያለባቸው ህፃናት ከወትሮው የተለየ እና ጮክ ብለው የሚያለቅሱ ሲሆን አልፎ አልፎ ከሚከሰተው ለቅሶ ውጭ ጡት በደምብ የሚጠቡና ሌላ የህመም ምልክት አይኖራቸውም ።
•  የህመሙ ምክንያት
• የህፃናት የሆድ ቁርጠት መንስኤ በውል ባይታወቅም ፤ ሆድ ውስጥ የአየር በብዛት ሲጠራቀም በሚከተለው የአንጀት ጡንቻዎች መኮማተር የህመሙ መንስኤ ሊሆን ይችላል የሚሉ መላ ምቶች አሉ።
• ይህ ህመም እስከ 6 ወር ባለ የህፃናት እድሜ ውስጥ በራሱ ጊዜ ይጠፋል ።

ህክምናው
• ወላጆች መረዳት ያለባቸው የሆድ ቁርጠት ምንም አይነት ፍቱን ህክምና እንደሌለው እና ህፃናት ላይ ለጊዜው ምቾት ከማንሳት ውጭ ለክፉ የማይሰጥ መሆኑን እድሜያቸው እየጨመረ ሲሄድ የሚቀንስ በኋላም የሚጠፋ ነው።

• ህፃንን ከፍ አድርጎ በተከሻ ይዞ ጀርባውን መታ መታ እንዲያገሳ ማድረግ ሆድ ውስጥ የተጠራቀመውን አየር እንዲያስወጣው ስለሚረዳ አንድ መፍትሔ ነው።
• በሚያለቅሱ ጊዜ ይዞ መንቀሳቀስ
• ሆድን ቀስ እያሉ መዳበስ
• ሞቅ ባለ ውሀ ገላን ማጠብ
• ዥዋዥዌ ማድረግ
• ዝቅ ያለ እና ለስላሳ የማያቋርጥ ድምፅ መልቀቅ
• የሚወዛወዝ አልጋ ላይ ልጁን ማስቀመጥ ፣ልጁን በቁመቱ ይዞ መንቀሳቀስ፣ ቀስ ብሎ መኪና እየነዱ ማንቀሳቀስ
• መድሀኒቶች ማለትም Phenobarbital የመሳሰሉ መድሃኒቶች መጠቀም ተገቢ አይደለም ከዚህም በተጨማሪ አሁን አሁን የሚመረቱ እና በህክምና ባለሙያዎች ጭምር የሚታዘዙ Herbal Medication (coliza drops,simiticon, gripes water እና  የመሳሰሉትን መድሃኒቶች መጠቀም በብዙ ጥናቶች የተረጋገጠ ስላልሆነ ባንጠቀም ጥሩ ነው፡፡

ወላጅ ከሆኑ የልጅዎ የሆድ ቁርጠት እርስዎን ለከባድ ጭንቀት እና መወጣጠር ውስጥ ሊከት ይችላል።በዚህ ሰዓት እርሰዎ ራቅ ብለው እረፍት መውሰድ አስፈላጊ ነው።

ቁርጠቱ እንዳይደጋገም የሚረዱ
• ህፃንን ጡት ወይም ጡጦ ካጠቡ በኋላ ማስገሳት
• ህፃንን ጡት ወይም ጡጦ በሚጠባበት ጊዜ ባዶ አየር እንዳይወስዱ መከታተል
• ህፃኑ በቂ ፈሳሽ እንዲያገኝ ማድረግ

ሌሎች ህፃናት የሚያለቅሱበት ምክንያት
• ሲርባቸው
• ዳይፐር ሳይመቻቸው ሲቀር (በእርጥበት ፣ ጠብቆ ሲታሰር)
• እንቅልፍ ሲፈልጉ
• የሰውነት ሙቀት ሲጨምር
• ብርድ