ሽንት ኩላሊት ደምን አጣርቶ የሚያስወጣው ክፍል ሲሆን 95% ውሀ 5% ኤሌክትሮላይቶች እና ቆሻሻዎች ናቸው ።
ጤናማ እና በቂ ፈሳሽ በሚዎስዱበት ጊዜ ሽንትዎ ብዙ የጎላ ቀለም በሌለው እና ነጣ ያለ ቢጫ ቀለም መካከል ነው፡፡በቂ ፈሳሾችን በማይወስዱበት ጊዜ ሽንትዎ ይበልጥ የተከማቸ ሲሆን ወደ ጠቆር ያለ ቢጫ ወይም የዓምበር ቀለም ይለወጣል ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የሽንት ቀለም እና መጠን እየዎሰዱ ያሉትን የውሀ መጠን ፣ ምግብ ፣ ቫይታሚን ጠቋሚ ነው።
የተወሰኑ ምግቦች ፣ አንቲባዮቲኮች ፣ የህክምና ሁኔታዎች እና ቀለሞች እንዲሁ ለጊዜው የሽንት ቀለም ይቀይራሉ ፡፡ ከዚህ ቀጥሎ የተለያዩ የሽንት ቀለም አይነቶች እና ምክንያቶች እናያለን ።
1. በጣም ነጭ ከሆነ ከመጠን በላይ ውሀ እየጠጡ እንደሆነ ያመለክታል ። ይህም የተለያዩ በደም ውስጥ የሚገኙ ንጥረ ነገሮችን በተለይም ፓታሽየም እና ሶድየም መጠናቸው እንዲያንስ ያደርጋል ይህም የልብ ጡንቻን ይጎዳል ።
2. ጥቁር ቢጫ - ይህም በቂ ውሀ እየወሰዱ እንዳልሆነ ወይም ኬቶን በሽንት ውስጥ መኖር ሊሆን ይችላል ። በቂ ውሀ አለመውሰድ ደግሞ ለኩላሊት ጠጠር ፣ የሰውነት ፈሳሽ መቀነስ ፣ የኤሌክትሮላይት መዛባት ያስከትላል ። ኬቶን የሚፈጠረው በቂ የሆነ ስኳር (glucose ) ሳያገኝ ሲቀር እና ቅባት (fat) ለሴሎች ጉልበት ሲጠቀም ነው ። ይህም በሽንት መልክ ይወጣል ። ከፍተኛ የኬቶን መጠን አደገኛ የስኳር በሽታ ጉዳትን (DKA) ተከትሎ ሊመጣ ይችላል ። አነስተኛ መጠን ከሆነ ለረጅም ጊዜ ካልተመገብን ሊከሰት ይችላል ።
3. ደማቅ ቢጫ - ከበቂ በላይ ሰው ሰራሽ ቫይተሚን ቢ እየወሰዱ ከሆነ
4. ቀይ- ይህ የሚፈጠረው ደም በሽንት ውስጥ ሲኖር ነው ። ይህም በኩላሊት ጠጠር ፣ የኩላሊት እና የሽንት ፊኛ ኢንፌክሽን ፣ የፕሮስቴት እጢ ካንሰር ፣ የኩላሊት ካንሰር ፣ ከባድ ስፓርት
5. ጥቁር ብርቱካናማ / ቡናማ - የጉበት ችግር ያመለክታል ። የጉበት ፣ የሀሞት ቀረጢትና የቱቦዎች ችግር ተከትሎ የቢሊሩቢን በደም ውስጥ መብዛት ጋር ተያይዞ የሚከሰት ነው።
6. ሀምራዊ - አነስተኛ ደም በሽንት ውስጥ ሲኖር ወይም ቀይ ስር ከበላን
7. ሰማያዊ - የካልስየም መብዛት /hypercalcemia
7. አረፋ ካለ - ፕሮቲን በሽንት ውስጥ መኖር ፤ ይህም የኩላሊት ቁስለት ፣ የኩላሊት ጠጠር ፣ የልብ እና የኩላሊት መድከም ፣ የተለያዩ የካንሰር አይነቶች
8. ብዙ የሚሸኑ ከሆነ - በሽንት ውስጥ የስኳር መኖር ነው ፤ ይህም የስኳር በሽታ ያመለክታል ።