አስም ለረጅም ጊዜ የሚቆይ የመንፈሻ አካል ህመም ሲሆን በማቁሰል ፣በማሳበጥና በማጥበብ ለመተንፈስ አሰቻጋሪ አስቸጋሪ ያደርጋል ።
አስም ተላላፊ ካልሆኑ በሽታዎች አነዱ ሲሆን እንደ የአለም ጤና ድርጅት ግምት በፈረንጆቹ አቆጣጠር 2016 አመተ ምህረት 339 ሚሊየን ሰዎች የአስም ህመም ተጠቂዎች ሲኖሩ 417,918 ሰዎች ደግሞ በዚህ ህመም ህይወታቸውን አጥተዋል ።
የአስም ምልክቶች
የአስም ምልክቶች በአሰም በሽታ ከሚከሰቱ ሶስት የአየር ቱቦ ሂደቶች ምክንያት የሚመጡ ናቸው
1.የአየር መመላለሻ ቱቦዎች መጥበብ ፦ በአስም ያልተጠቃ ሰው በአየር ቱቦ ዙሪያ ያሉ ጡንቻዎች ላላ ያሉና የአየር ዝውውር በቀላሉ ይካሄዳል ነገር ግን አስም በሚኖርበት ጊዜ እነዚህ ጡንቻዎች ይጠብቁና የአየር ቱቦዎችን እንዲጠቡ በማድረግ የአየር ዝውውሩን ከባድ ያደርጉታል ።
2.የአየር ቱቦዎች ቁስለት ፦በሌላ በኩል አስም የአየር ቱቦዎችን እብጠት፣ቁስለትና ቁጣን በማስከተል ሳንባን ይጎዳል ።
ይህን ማከምም በረጅም ጊዜ አስምን ለመቆጣጠር ይረዳል።
3.የአየር ቱቦ ቁጣ፦ ሌላው ምክንያት የአስም ተጠቂ የሆኑ ሰዎች የአየር ቱቦ በጣም ቁጡና ቀላል እና አነስተኛ ለሆኑ የአስም ህመም ቀስቃሾች የሚቆጣና ከተገቢው በላይ የሆነ መልስ ይሰጣል ።
በእነዚህ ምክንያቶች የተነሳ የሚከተሉት ምልክቶች ይታያሉ፦
•ሳል፦በተለይም ጧትና ማታ ላይ የሚጨምር
•በሚተነፍሱበት ጊዜ ከሳንባ የሚነሳ በተለይም አንገት አካባቢ የፉጨት ድምፅ መስማት
•ለመተንፈስ መቸገር
•ደረት አካባቢ ጥብቅ አድረጎ መያዝ ፣የደረት ህመም
•ቶሎ ቶሎ መተንፈስ
•በትንፋሽ ማጠር ምክንያት ለመተኛት መቸገር
መቸ ወደ ህክምና መሄድ አለብዎት
•ለመጀመሪያ ጊዜ ከላይ ከተጠቀሱት ምንም አይነት ምልክት ካለ
የአስም ህክምና እየተከታተሉ ከሆነ
•ቶሎ ቶሎ መተንፈስ
•የፊት እና የከንፈር መገርጣት/ሰሰማያዊ መምሰል
•ሲያወሩ፣ሲተነፈፍሱ፣ሲራመዱ አየር ማጠር
•በሚተነፍሱበት ጊዜ የደረት ቆዳ ወደውስጥ መግባት
•በህክምና ላይ ሁነው ምልክቶቹ •በሚወስዷቸው መድሀኒቶች አለመመለስ
መድሀኒት የሚወስዱበት ብዛት መጨመር
የአስም ማገርሸት
አስም አገረሸ የሚባለውየአስም ምልክቶች በድንገት ሲባባሱና ለመተንፈስ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ሲፈጥሩ ነው።
እያንዳንዱ ሰው ወይም አንድ ሰው በተለያየ ጊዜ የተለያየ የአስም ማገርሸት ምልክት ሊኖረው ይችላል ።
ህመሙ እየተባባሰ መሆኑን የሚያቁባቸው ምልክቶች
•ምልክቶች ብዙ ጊዜ የሚመጣና የእለት ከለት እንቅስቃሴዎን/ሰራ የሚያስተጓጉል ከሆነ
•ለመተንፈስ መቸገር፣የደረት ህመም
•ህመሙን ለማስታገስ ከድሮ በተለየ ደጋግመው መድኀኒት መውሰድ ካስፈለገ
የተለያዩ የአስም አይነቶች አሉ
1.የህፃናት አስም፦አስም ብዙ ጊዜ የሚጀምረው በህፃንነት ሲሆን በአማካይ 3 አመት ነው።
አስም በሚነሳበት የተለያየ ጊዜ የተለያየ ምልክት ሊኖረው ይችላል ምልክቶቹም ቀለል ያሉና ለመለየት አስቸጋሪ ሊሆኑ ይችላሉ ፤ ለምሳሌ ፦
በሚጫወቱበት ጊዜ፣በማታ እና በሚስቁበት ጊዜ የሚነሳ ሳል
ቶሎ ቶሎ መተንፈስ
ከአቻዎቻቸው ጋር ሲጫወቱ ቶሎ መድከም
በደረት ውሰጥ ሚሰማ የፉጨት ድምፅ
2.በአዋቂነት የሚጀምር አስማ
3.ከአለርጅ ጋር የተያያዘ አስማ፦ ይህም የቆሻሻ ፣የአበባ ፣የቤት እንስሳት ቆዳ ብናኝ ሊያስነሳው የሚችል
4.ከስራ ቦታ ጋር የተያያዘ
5.ከእንቅስቃሴ ጋር የተያያዘ
አስም የሚቀሰቅሱ ነገሮች
•ሳይነስ፣ጉንፋንና ሌሎች የሳንባ ህመሞች
•የአበባ ፣የእንስሳት ቆዳ፣የፈንገስ፣ የአቧራ ብናኞች
•ከባድ ሽታ ያላቸው እንደ ሽቶ፣ አልኮል ፣ለማፅዳት የሚያገለግሉ ፈሳሾች
•የየር ብክለት
•የሲጋራ ጭቀዝቃዛ አየር
•ከባድ ስሜት፦ጭንቀት ፣ድብርት፣ሀዘን
ምግብና መጠጥ •አሳ፣ቆምጣጤ፣ቢራ፣ወይን፣የታሸገ ጭማቂ
ምርመራ
•ስፓይሮሜትር፦ ምንያህል አየር ከሳንባ እንደሚወጣና በምንያህል ፍጥነት እንደሆነ የመመለካ
•ራጅ፣የደም ምርመራ፣የቆዳ አለርጂ ምርመራ
ህክምና
የአስም ህክምና የታካሚውን ሙሉ ተሳትፎ የሚጠይቅ ስለሆነ ከሀኪምወ ጋር በመሆን የህመሙን የመቆጣጠር እቅድ ያውጡ።
1.አስምንን የሚቀሰቅሱ/የሚያስነሱ ነገሮችን ማስወገድ (Avoidance Measures )
•ከድመት፣ከውሻ ጋር ያለውን ንክኪ ያስወግዱ
•አያጭሱ፣ከሚያጨስ ሰው ይራቁ
•የአበባ ብናኝ ፣የቤት ቆሻሻ ብናኝ ያስወግዱ
•ሳኒታይዘር ፣ ሽቶ ያስወግዱ
•ክብደትን መቆጣጠር
•እንቅስቃሴ አዘውትሮ መስራት
•የአተነፋፈስ እንቅስቃሴ መስራት
2.የመድሀኒት ህክምና (pharmacotherapy )
ሁለት አይነት የአስም መድሀኒት ቡድኖች ሲኖሩ በአጭር ጊዜ የአስም ህመም ምልክቶችን የሚያስታግሱና በረጅም ጊዜ የአስም ህመም ለመቆጣጠር የሚረዱ ናቸው።
የሚነፋና በአየር ቧንቧ ተስቦ ለመሄድ የሚሰጡበት መንገድ ገፍተኛ መድሀኒት ወደሳንባ ለማድረስና የጎንዮሽ ጉዳትን ለመከላከል ይረዳል ።
የአስም መድሀኒቶች እንደ ህመሙ የመቆጣጠር መጠን መቀነስ እና መጨመጠር ያለባቸው ሲሆን ከከፍተኛ ተነስቶ እየቀነሱ መሆድ ህመሙን ቀቶሎ ለመቆጣጠር ይረዳል።
ከመድሀኒቶቹ
1.የአየር ቱቦን የሚያሰፍ (Bronchodilators)
2.ስቴሮይድ
3.ቁስለትን የሚቀንሱ (anti-inflammatory )
3.አጋዝ ህክምና (supportive therapy)
ኦክስጅን
የአስም ህመም የሚያስከትላቸው ችግሮች
•ድካም
•ከስራ መስተጓጎል
•የአእምሮ ህመም
•የሳንባ ምች እና ሌሎች የሳንባ በሽታዎች መጨመር
•የተደጋጋሚ ሆስፒታል ህክምና
•የሳንባ ስራ ማቆም
አስም እና ኮቪድ-19
አስም የመተንፈሻ አካል ህመም እንደመሆኑ ምልክቶቹን መቆጣጠር ካልተቻለ ለከባድ የኮሮና በሽታ ሊያጋልጥ ይችላል ።