የሕጻናት ጤናማ አመጋገብ ( ከ6 ወር - 2 ዓመት)
# ህፃናት 6 ወር ከሞላቸው በኋላ የእናት ጡት ወተት ለብቻው የምግብ ፍላጎታቸውን ስለማያሟላ ተጨማሪ ሌሎች ምግቦችን መጀመር ይኖርባቸዋል ::
# በዚህ የእድሜ ክልል ህፃናት እድገታቸው ፈጣን ስለሚሆን በቂ የሆነ ምግብ ካላገኙ ለስውነታቸው የሚሆን በቂ ኃይል (calorie) አያገኝም። በተጨማሪም ሰውነታቸው ለመቀጨጭ እና መቀንጨር ይዳረጋል ::
# በተጨማሪም የበሽታ የመከላከያ ሀይላቸው (Immunity) ዝቅተኛ ስለሚሆን ለተለያዩ ኢንፌክሽኖች ተጋላጭ ይሆናሉ::
# ሕጻናት ከ 6 ወር በፊት ሌሎች ምግቦችን ቢጀምሩ ችግር ይኖረዋል?
አዎን! ከ6 ወር በፊት ሌሎች ምግቦችን መጀመር ለተቅማጥ እና ትውከት: የጡት ወተት መቀነስ እና የመሳሰሉት ችግሮችን ያስከትላል።
# ሕጻናት ተጨማሪ ምግቦችን ዘግይቶ ቢጀምሩ ጉዳቱ ምንድነው?
ህፃኑ በቂ የሆነ ክብደት እንዳይጨምር እና የተለያዩ ንጥረ ነገሮች (minerals) እና ቫይታሚን እጥረት እንዲያጋጥመው ያደርጋል። ይሄም የራሱ ከሆነ ከፍተኛ የጤና ችግርን ያመጣል::
# ከ6 ወር - 2 ዓመት ያሉትን ህፃናት ምን እንመግባቸው?
በየትኛውም የእድሜ ክልል ዉስጥ ያሉ ህፃናትም ሆነ አዋቂዎች የተመጣጠነ ምግብ መመገብ ይኖርባቸዋል:: የተመጣጠነ ምግብ ማለት መሰረታዊ የሆኑ የምግብ ክፍሎችን የሚያካትት ነው:: እነሱም የእህል ዘር፣ ጥርጣሬ፥ አትክልት፥ ፍራፍሬ፥ ወተት እና የወተት ምርቶች፥ እንቁላል እና ስጋ ናችው::
ከላይ የተጠቀሱት ን የምግብ አይነቶች በተለያየ መንገድ ማዘጋጀት ይቻላል:: በሀገራችን የተለመደው አሰራር የምጥን ዱቄት ይባላል:: ይሄም በውስጡ የተለያዩ ከእህል ዘሮችን ማካተት ይቻላል ለምሳሌ 3 እጁ ከእህል ዘሮች ማለትም የተፈተገ ስንዴ ÷በቆሎ ÷ማሽላ ÷ጤፍ ÷አጃ እና የመሳሰሉት አድርጎ አንድ እጁን ደሞ ከጥራጥሬ አይነቶች ደሞ ባቄላ ÷ሽንብራ÷ አተር÷ ምስርን ÷ኦቾሎኒ ማካተት ይኖርበታል::
ለልጅዎ ምግብ ስጀምር ምን ያህል ነው መስጠት ያለብዎ?
ከ 6 - 8 ወር : በቀን 2 - 3 የቡና ሲኒ ☕️
ከ 9 ወር - 1 ዓመት : 4-5 የቡና ሲኒ☕️
ከ 1 ዓመት በላይ ግን በ ሲኒ መለካት አስፈላጊ አይደለም ሆኖም ግን 3 ዋና ዋና የምግብ ሰዓቶችን ጠብቆ በመስጠት በተጨማሪ ደሞ በ መሃል በመሃል 2 መክስሶችን መስጠት ይገባል::
# እድሜያቸዉ 6 - 8 ወር ላሉ ህፃናት ከአጥሚት ትንሽ ወፈር ያሉ ምግቦች ይመከራሉ ::
#እድሜያቸው 8-12 ወር ለሆናቸዉ ደሞ በከፊል ጠጣር(semi solid) ወይም ለስለስ ያለ ገንፎ በቀን 4-5 ጊዜ መመግብ ይኖርባቸዋል፡፡
በዚህ የእድሜ ክልል ላሉ ህፃናት ምግብ ስንጀምር የታሸጉ ምግቦችን(Processed food) ትተን በተፈጥሮ ከእህል ዘሮች ከተዘጋጁ እና በተለመዶው ምጥን ከሚባሉ ምግቦች ብንጀምር መልካም ነው:: እነዚህ ምግቦች በቀላሉ የሚፈጩ እና በዉስጣቸው ከፍ ያለ የብረት ማእድን ስለሚይዙ የደም ማነስን ይከላከላሉ ። በተጨማሪም ኃይል ሰጪ (carbohydrate) እና ገንቢ(protein) የሆኑ ምግቦች ናቸው::
ልጆች የእህል ዘሮችን ከለመዱ በዋላ በስለዉ የተፈጩ አትክልቶችን ቀስ በቀስ ማስለመድ ተገቢ ነው::
በመቀጠልም የተፈጨ አቦካዶ ሙዝ ፓፓያ ካስለመዱ በኋላ ቀስ በቀስ ደሞ እንቁላል እና የተፈጨ ስጋ መስጠት ይቻላል ።