አዮዲን በጣም አስፈላጊ ከሆኑና ትሬስ ኤለመንት ተብለዉ ከሚጠሩ ማዕድናት የሚመደብ ሲሆን በታይሮይድ፣ ታይሮክሲንና ትራይአዮዶታይሮኒን ሆሮሞኖች ዉስጥ ይገኛል፡፡
አዮዲን ለታይሮይድ እጢ ጤንነት፣ ለሰዉነታችን ነርቮች ጤንነት እንዲሁም ለመራቢያ አካላት ጤንነት አስፈላጊ የሆነ ማዕድን ነዉ፡፡ ይህ ማእድን ለአንጎል ስራ፣ ለስረዓተ ምግብ መፈጨት ወይም ሜታቦሊዝም፣ ለእርግዝናና ፅንስ እድገት አስፈላጊ ለሆነዉ ታይሮይድ ሆርሞንን ለመስራት ወይም ለማዘጋጀት አስፈላጊ ነገር ነዉ፡፡
የአዮዲን የጤና ጥቅሞች
1.ሆርሞንን ለመቆጣጠር ወይም ሬጉሌት ለማድረግ
2.ለልብ ጤንነት
3.ለጤናማ ቆዳ
4.መርዛማ ነገሮችን ለማስወገድ
5.ካንሰርን ለመከላከል
6.እንቅርትን ለመከላከል
7.ለጤናማ እርግዝና
8.የበሽታ መከላከል እቅምን ለማጎልበት
9.ለአእምሮ እድገት
10.የሰዉነት ሀይልን ለመገንባትና
11.ለጤናማ ፀጉር ይጠቅማል፡፡
ጥሩ የአዮዲን ምንጭ የሆኑ ምግቦች
1.የባህር ምግቦች ፡- አሳ (እንደ ኮድና ቱና )፣ ሽሪምፕና ሌሎች የባህር ምግቦች
2.የወተት ተዋፅኦዎች፡- ወተት፣ እርጎና አይብ
3.በአዮዲን የበለፀጉ ምግቦች ለምሳሌ አዮዳይዝድ ጨዉ
4.እንቁላል በተለይ የተቀቀለ እንቁላል፣ በጣም ትሩ የሆኑ ምንቾች ሲሆኑ እንደ
5.ሽንከርት፡ ነጭና ቀይ ሽንኩርቶች
6.ሙዝ፣ እስትሮቤሪ፣ ስኳር ድንች እንዲሁም
7.በቆሎ፣ አተርና ኦቾሎኒ የመሳሰሉት ደግሞ መጠነኛ የአዮዲን ምንጮች ናቸዉ፡፡