እንዴትስ ማቆም እንችላለን?
ስቅታ በአዋቂም ሆነ ልጆች ላይ ሊታይ የሚችል ብዙ ጊዜ ጤናማ እና ተፈጥሯዊ ምላሽ(reflex)ነው።
አዋቂ ሰዎችን እንደሚረብሽው ግን ህፃናትን ብዙ ጊዜ አይረብሻቸውም። እንደውም ህፃናት ስቅ እያላችው ጥሩ እንቅልፍ መተኛት ይችላሉ ::
ስቅታ የሚመጣው እንዴት ነው?
ስቅታ የሚከሰተው ዲያፍራም የሚባለው ሳንባችን ከታች ደግፎ የሚገኘው ጡንቻ ድንገት ስኮማተር እና ቮካል ኮርድ የሚባለው የአየር መግቢያ ድንገት ሲዘጋ ነው::
የልጆች ስቅታ መንስኤው ምንድነው?
1.ቶሎ ቶሎ እና ብዙ ምግብ መመገብ: ቶሎ ቶሎ ብዙ ጡት ወይም ጡጦ መጥባት። ይህም ብዙ አየር ወደ ጨጓራ እንዲገባ እና ዲያፍራም የሚባለው ሳንባችን ከታች ደግፎ የሚገኘው ጡንቻ ድንገት እንዲኮማተር ያደርጋል::
2.ህፃናት የሚያስደስታቸውን ወይም ለየት ያለ ነገር ሲያገኙ( excitement)
3. ህፃናት ሙቀት በተለይ ሆድ አካባቢ ያለ ሙቀት በድንገት መቀነስ እና የመሳሰሉት ናቸው።
መፍትሄው ምንድነው?
1. ጡት ወይም ጡጦ ከጠቡ በኋላ በደንብ ማስገሳት። የአሜሪካ የህፃናት ሕክምና ማህበር አንድ ህፃን ከ60 ሚሊ ሊትር በላይ ከጠባ በደንብ ማስገሳት እና ልጁን ከ 20-30 ደቂቃ ቀና አድርጎ(upright position) ማስቀመጥን ይመክራል::
2.ልጆች በጣም ሳይርባቸው መመገብ ወይም ማጥባት መሃል ላይ ስቅታ ከጀመራቸው ማጥባቱ ቆም አድርጎ ማስገሳት እና ትንሽ ቆይቶ ማጥባት
3. የእንጀራ እናት(Pacifier, dummy) መስጠት።
ይህ መፍትሄ እድሜያቸው ከ1 ወር በታች ላሉ ህፃናት እና ባጠቃላይ እንደኛ ላሉ ሃገራት ላይ ከንፅሕና ጋር ተያይዞ ብዙም አይመከርም። ሆኖም ልጅን ለማረጋጋት ተብሎ እንደ አማራጭ ይቀርባል
4. ዋናው መፍትሄ ግን ወላጆች ስቅታ ቀላል እንደ ሆነ ልጁ ላይ ጉዳት እንደማያደርስ ማወቅ እና 5-10 ደቂቃ ዉስጥ እንደሚቆም ማወቅ እና በመረጋጋት ልጃቸውን ማጫወት ማዝናናት አለባቸው:: ከዚህ ዉጭ ያሉት ባህላዊ መንገዶችን ባንጠቀም ይመከራል።
ስቅታ መቼ ነው መታከም ያለበት?
1.የተከሰተው ልጁ 1 ዓመት እድሜ በላይ ከሆነ እና ስቅታው በጣም ተከታታይ ከሆነ
2.ህፃኑ እድሜው ከ 1 ዓመት በታች ሆኖ ከ ስቅ ታው ጋር ተደጋጋሚ ትውከት ቅርሻት ሳል እና መነጫነጭ ካለው ምን አልባት ከ ጨጓራ ጋር ሊያያዝ ይችላል ። በዚህ ጊዜ ሐኪምን ማማከር ተገቢ ነው::
መረጃውን አንብበው ሼር ያድርጉ
ዶክተር ፋሲል መንበረ በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ የሕጻናት ስፔሻሊስት ሐኪም