የሆድ ድርቀት ለመከላከል የሚረዱ ዘዴዎች
? ውሃ መጠጣት፡- በሰውነታችን ውስጥ ያለው የውሃ መጠን ሲቀንስ የሆድ ድርቀት ሊያስከትል ይችላል፡፡ ስለዚህ በቀን ውስጥ በቂ ውሃ መጠጣት የሆድ ድርቀትን ይከላከላል፡፡ ሴቶች በቀን ከ8-9 ብርጭቆ ውሃ እና ወንዶች ደግሞ በቀን ከ9-10 ብርጭቆ ውሃ ቢጠጡ ተብሎ ይመከራል፡፡
? በፋይበር የበለፀጉ ምግቦች መመገብ፡- በምግቦች ውስጥ የሚገኝ ፋይበር የሚባል ቃጫ መሰል ንጥረ ነገር አለ፡፡ ፋይበር በሁለት ይከፈላል
- የማይፈጭ ፋይበር፡- ሳይፈጭ በሰውነታችን ውስጥ የሚያልፍ ሲሆን ሰገራን የማለስለስ እና ከበድ እንዲል እና ከሰውነታችን ቶሎ እንዲወገድ የማድረግ ባህሪ አለው፡፡
- የሚፈጭ ፋይበር፡- እንደዚህ አይነት ፋይበር በሚፈጭበት ጊዜ ከውሃ ጋር ይቀላቀላል እና ጄል ወደ ሚመስል ነገር ሰውነታችን ውስጥ ይቀየራል ይሄም ሰገራችን በቀላሉ እንዲወገድ ይረዳል፡፡
? አፕል ወይም ፖም መመገብ፡-አፕል ውስጥ መፈጨት የማይችለው የፋይበር አይነት በብዛት ይገኛል፡፡ ይሄ አይነት ፋይበር ሰገራችን ቶሎ በሰውነታችን አልፎ እንዲወጣ ያግዘዋል፡፡ በተለይ አፕሉን ሳይላጥ መብላት ነው ያለብን፡፡
? አሲድነት ያላቸው ፍራፍሬዎች፡- ቆምጠጥ ያሉ ፍራፍሬዎች ማለት እንደ ብርቱካን፣ አናናስ ወይም ሎሚ ያሉት ናቸው፡፡ እነዚህ ፍራፍሬዎች በሁለቱም አይነት ፋይበር የበለፀጉ ስለሆነ የሆድ ድረቀትን ለማስታገስ ይጠቅማሉ፡፡
? አረንጓዴ ቅጠል ያላቸው አትክልቶች፡- እንደ ሰፒናች፣ ብሮኮሊ የመሳሰሉት አረንጓዴ ቅጠል ያላቸው አትክልቶች ከፋይበር በተጨማሪ ቫይታሚን ኬ፣ ቫይታሚን ሲ እና ፎሌት የመሳሰሉትን ለጤናችን አስፈላጊ የሆኑ ንጥረ ነገሮች ይዘዋል፡፡ በእነዚህ አትክልቶች ውስጥ ያለው ፋይበር ሰገራን በማለስለስ የሆድ ድርቀትን ይከላከላል፡፡
? ስኳር ድንች፡- አንድ መካከለኛ የስኳር ድንች በውስጡ 3.8 ግራም የሚያህል ፋይበር ይይዛል፡፡ ስለዚህ የሆድ ድርቀትን ለመከላከል ተመራጭ ምግብ ነው፡፡
? ባቄላ፣ ምስር እና አተር፡- እነዚህ የማይፈጨውን እና የሚፈጨውን ፋይበር በብዛት ይዘዋል፡፡
? የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ፡- ቀለል ያለ የአካል ብቃት እንቅስቃሴን በሳምንት ውስጥ ለ3 ቀናት ቢያንስ ለ30 ደቂቃ ማድረግ ሰገራ ከአንጀታችን ውስጥ ቶሎ እንዲያለፍ ይረዳዋል፡፡ ነገር ግን በጣም ከባድ የሆኑ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን ማድረግ ለሆድ ድርቀት ሊያጋልጠን ስለሚችል ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርብናል፡፡ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን ስናደርግ ውሃ በደንብ መጠጣት ይኖርብናል፡፡