ኪንታሮት ለበሽታው በትክክል ገላጭ ስም ባይሆንም፤ የኪንታሮት በሽታ በፊንጢጣ እና በታችኛውየአንጀት ክፍል የሚገኙ የደም መላሽ ስሮች መላላትና መለጠጥ እንዲሁም በደም በመወጠር ማበጥ ነው፡፡
ኪንታሮች በአንጀት ታችኛው ክፍል ሲፈጠር የውስጥ ኪንታሮት ሲባል በፊንጢጣ ላይ ከሆነ ደግሞ የውጪ ኪንታሮት ይባላል፡፡
በእድሜ ዘመን ከአራት አዋቂዎቸወ ሶስቱ (75%) የኪንታሮት በሽታ ሊያዛቸው ይችላል። ኪታሮት የተለያዩ ምክንያቶች ሊኖረው ይችላል፡፡ በአብዛኛው ግን የሚታወቅ አይደለም፡፡
ብዙ ውጤታማ የህክምና ዘዴዎች እንዲሁም ጤናማ የአኗኗር ዘይቤ ለበሽታው መፍትሔ የሚሆኑ ናቸው ፡፡
ምልክቶቹ የትኞቹ ናቸው?
• ፊንጢጣ አካባቢ መብላት
• ህመም ወይም አለመመቸት
• ፊንጢጣ አካባቢ እብጠት
• ይሄኛው አይነት የታችኛው የአንጀት ክፍል ላይ ስለሚወጡ ማየትም መዳሰስም አይቻልም፡፡ ብዙውን ጊዜ ህመም አይኖራቸውም፤ ነገር ግን ሰገራ በሚያልፍ ጊዜ የሚኖር ማማጥ እና መቆጣት ምልክቶች ሊያሳይ ይችላል፡፡
• ደም የቀላቀለ ሰገራ
• ኪንታሮቱ በፊንጢጣ በኩል ከወጣ ህመም እና መቆጣት ይኖራል
• ደም የቋጠረ የውጭ ኪንታሮት ከፍተኛ ሀመም፣ እብጠት፣ መቆጣት እና ፊንጢጣ አካባቢ እባጭ ሊያመጣ ይችላል፡፡
በምን ምክንያት ይመጣል?
• ፊንጢጣ አካባቢ ያሉ የደም ስሮች በግፊት ውስጥ ሲሆኑ የመለጠጥ እና የማበጥ ባህሪ አላቸው፡፡ ኪንታሮት የሚፈጠረው በታኛው የአንጀት ክፍል ላይ ከፍተኛ የሆነ ግፊት ሲኖር እና የሚከተሉት ካሉ ነው፤
• በመፀዳዳት ወቅት ማማጥ
• ለረጅም ሰዓት ሽንት ቤት መቀመጥ
• ለረጅም ጊዜ ተቅማጥ ወይም ድርቀት ሲኖር
• ከልክ ያለፈ ውፍረት
• እርግዝና
• የፋይበር መጠኑ ዝቅተኛ የሆነ ምግብ መውሰድ
• ለብዙ ጊዜ ክብደት ማንሳት
ተጋላጭነት
• ከእድሜ ጋር የኪንታሮት ተጋላጭነት ይጨምራል፡፡ ምክንያቱም ከእድሜ ጋር ተያይዞ በፊንጢጣ እና በታኛው የአንጀት ክፍል የሚገኙ የደም ስሮች ይደክማሉ፡፡ በእርግዝናም ወቅት የፅንሱ ክብደት በፊንጢጣ አካባቢ የሚኖረውን ግፊት ስለሚጨምረው ተመሳሳይ ለውጦች ይኖራሉ፡፡
ኪንታሮት ምን ሊያመጣ ይችላል?
• ደም ማነስ - ብዙ ደም የሚፈስ ከሆነ
• ኪንታሮቱ የደም ምንጩ ከተቋረጠ እጅግ ከፍተኛ ህመም
• የደም መርጋት
እንዴት እንከላከለው?
• ዋነኛው የመከላከያ መንገድ ሰጋራን ለስላሳ በማድረግ በቀላሉ እንዲያልፍ ማድረግ ነው፡፡
ኪንታሮትን ለመከላከልና ምልክቶችን ለመቀነስ የሚከተሉት ይመከራሉ፤
• በፋይበር የበለፀጉ ምግቦችን መመገብ
• ፈሳሽ ነገሮችን በሚገባ መውሰድ
• የፋይበር ሰፕሊመንቶችን መውሰድ
• በሚፀዳዱ ወቅት አለማማጥ
• ለመፀዳዳት በፈለጉ ጊዜ ሳይቆዩ መፀዳዳት
• አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ
• በአንድ ቦታ ለረጅም ጊዜ አለመቀመጥ
ምርመራ
• ሀኪሞት በማየት የውጭ ኪንታሮትን ሊመረምር ይችላል፡፡ ለውስጥ ኪንታሮት ደግሞ ንፁህ ጓንት በመጠቀም ማረጋገጥ ይቻላል፡፡
ሀኪሞት የሚከተሉት ካለቦት ግን ሁሉንም የአንጀት ክፍል በፊንጢጣ በሚገባ መሳሪያ ሊመረምር ይችላል፤
• ያሎት ምልክቶች የሌላ የአንጀት በሽታ ምልክት ጋር ተመሳሳነት ካለው
• ለአንጀት ካንሰር ተጋላጭ ከሆኑ
• እድሜዎት ከ45 በላ ከሆነ
ህክምና
• በፋይበር የበለፀጉ ምግቦችን መውሰድ
• የሚቀቡ መድሀኒቶችን መጠቀም
• ለብ ያለ ውሀ ላይ ትንሽ ጨው በማድረግ ፊንጢጣ አካናኒ ማጠን
• ህመም ማስታገሻ መውሰድ
• ቀዶ ህክምና