ከክትባት በኋላ ክትባቱ እየሰራ እንደሆነ የሚጠቁሙን መለስተኛ ምልክቶች አሉ፡፡
እነዚህ ምልክቶች የህጻናት ሰውነት አዲስ ፀረ እንግዳ አካላትን መኖሩን የሚጠቁሙ እና በአማካኝ እስከ ሶስት ቀን ሊቆዩ የሚችሉ ምልክቶች ናቸው፡፡
☑️ ሊኖሩ የሚችሉ ምልክቶች
? የተወጉበት ቦታ ላይ መቅላት እና የህመም ስሜት
? የተወጉበት ቦታ ላይ አነስተኛ እብጠት
? ማልቀስ እና መነጫነጭ
? መጠነኛ ትኩሳት
? ማስመለስ
? የምግብ ፍላጎት መቀነስ
☑️ ምልክቶች እንዳይባባሱ መደረግ ያለባቸዉ ነገሮች
? በማባበል እና በማጫወት ሃሳባቸውን ለመስረቅ መሞከር
? የተወጉበትን ቦታ አለመንካት
? ቶሎ ቶሎ ጡት ማጥባት ወይም ትንሽ ትንሽ ቶሎ ቶሎ መመገብ
? ትኩሳቱን በመለካት ከ37.5 °C በላይ ከሆነ ንጹህ ፎጣ ቀዝቃዛ ዉሃ ዉስጥ በመንከር ለማቀዝቀዝ መሞከር የማይበርድ ከሆነ የትኩሳት ማብረጃ መድሐኒቶችን መስጠት
☑️ መቼ ባለሙያ ማማከር አለብኝ?
↪️ የትኩሳት ማብረጃ መድሐኒት ተወስዶ ትኩሳት የማይቀንስ ከሆነ
↪️ ሙሉ ለሙሉ የመጥባት ወይም የመመገብ አለመቻል
↪️ በተደጋጋሚ ማስመለስ ካለ
↪️ የቆዳ ከለር መቀየር ካለ/ነጭ የመሆን/
↪️ አቅም ማጣት/የተባባሰ የድካም ስሜትየሰዉነት ማንቀጥቀጥ
↪️ ትንፋሽ ማጠር/ቶሎ ቶሎ መተንፈስ
↪️ የልብ ምት መጨመር
ዶክተር መሐመድ በሽር የህፃናት እስፔሻሊስት