ካንሰር (cancer) ምንድን ነው?

ካንሰር የሴሎቻችን ደህንነት በሚቆጣጠሩ የዘረመል(genetics) ለውጥ የሚመጣ በሽታ  ነው። ሰውነታችን ብዙ ትሪሊየን በሚሆኑ  ህዋሳት(cells)  የተሰራ ነው።

በእያንዳንዱ ህዋስ (cell) ውስጥ የሚገኝ ጂን (gene) ደግሞ ሴሎች አንዲያድጉ ፣ አንዲሰሩ ፣ እንዲባዙና እንዲያድጉ ያዛል። ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ ከአንዳንድ ጂኖች የሚመነጭ ትእዛዝ ሴሎችን ባልተለመደ ሁኔታ አንዲሰሩ ያደርጋቸዋል። ይህም ባልተለመደ ሁኔታ ይከፋፈሉና ያድጋሉ። ከዚያም ቁጥጥር በሌለዉ መንገድ ይራባሉ ከጊዜ በዃላም በአንድ ላይ የተሰበሰቡ የተናጉ ሴሎች እብጠትን ፣ አጢን (tumor) ይፈጥራሉ።
የካንሰር መነሻ የሰውነት ክፍሎች ምን ምን ናቸው?
• ከ100 በላይ የካንሰር አይነቶች አሉ።
• ካንሰር ከማንኛውም የሰውነት ክፍል ውስጥ ሊጀምር ይችላል። በተለይም የጡት ፣ የሆድ እቃ ፣ የፊኛ ፣ የሰንባ ፣ የቆዳ ፣ የጉበት ፣ የማህጸን በር ፣ የመሳሰሉት እያልን ልንከፉፍላቸው እንችላለን።
እንዴት በካነሰር ሊያዙ ይችላል?
• ካንሰር በማንኛውም ሰው ፣ በማንኛውም እድሜ ላይ ሊከሰት ይችላል።
• ካንሰር የሚያመጡ የዘረመል ለውጦች (genetic changes) ከወላጆቻችን ልንወርሰው (inherit)  ልናደርገው እንችላለን።
• ሰዎችን ለበለጠ ለከፍተኛ ለካንሰር የሚያጋልጡን ነገሮች አሉ ለምሳሌ ሲጋራ ማጨስ ፣ ከመጠን በላይ አልኮል መጠጥ መጠጣት ፣ እድሜ እየገፋ ሲሄድ ፣ የአካል ብቃት  እንቅስቃሴ አለማድረግ ፣ ከመጠን በላይ መወፈር ፣ ከቤተሰብ የሚመጣ ፣ አንዳንድ ኬሚካሎች ለምሳሌ አሰቤስቶስ (asbestos) ፣ አፍላቶክሲን (aflatoxin) በተለያዩ የተበላሸ ለዉዝ ፣ ሩዝ ፣ በቆሎ ውስጥ የሚገኝ ፣ ቫይረሶች ለምሳሌ human papilloma virus ፣ ሄፓታይቲስ (hepatitis virus) ፣ ጨረር (radiation)
ካንሰር በሽታ ከሰው ወደ ሰዉ ይተላለፋል?
• ካንሰር ተላላፊ በሽታ አይደለም። ካንሰር  ካለበት ሰው ጋረ መሆን ፣ መነካካት ፣ መሳሳም ፣ በትንፋሽ ሊተላለፍ አይችልም።
መቼ ነው የህክምና እርዳታ ማግኘት ያለብን?
• የማያቋርጥ ሳል ፣ የትንፋሽ ማጠር ፣ የድምፅ መቀየር
• የአይን ቢጫ መሆን ፣ የሆድ እብጠት ፣ የምግብ ፍላጎት መቀነስ ፣ ምክንያቱ ያልታወቀ የክብደት መቀነስ ፣ የማያቋርጥ ማቅለሽለሽ እና ማስመለስ
• በጡት አካባቢ ያልተለመዱ ለውጦች ፣ የጡት ቀለም መቀየር ፣ ህመም ወይም እብጠት ፣ በጡት ጫፍ  አካባቢ ፈሳሽ ካለ ወይም የጡት ጫፍ ወደ ውስጥ ከገባ
• ከሴቶች ብልት የደም መፍሰስ ፣ በግብረ ስጋ ግንኙነት ጊዜ ህመም ስሜት መኖር ፣ ከብልት አካባቢ ፈሳሽ መኖር
• ያልተለመደ የቆዳ ቀለም መቀየር ፣ የቆዳ ጥቁር ነጠብጣብ መኖር አንዲሁም ሽታ ያለው የሚያመረቅዝ ያልዳነ ቁስል
ከላይ የተጠቀሱት በሌላ የጤና ችግር ምክንያትም ሊሆን ይችላል?
ካንሰር በሰውነት ክፍላችን ሊሰራጭ ይችላል?**
• አንድ ሰው  ካንሰር ከተያዘ በዃላ ከጀመረበት ቦታ አነስቶ በአቅራቢያው የሚገኘውን አካል ወይም በደም ዝውውር (blood stream) ወይም በፍርንትት (lymph node) አመካኝነት በተለይ ወደ ሳንባ ፣ ጉበት ፣ አጥንት አንዲሁም ወደ ጭንቅላት ሊሰራጭ (metastasize) ሊያደረግ ይችላል።
• ስለዚህ ቀደም ብሎ የቅድመ ካንሰር ምርመራ ማድረግ እጅግ በጣም ጠቃሚ ነው።
ህክምናውስ ምንድን ነው?
• ኬሞቴራፒ (ፀረ ካንሰር መድሀኒት በመጠቀም) ፣ ራዲዮቴራፒ (የጨረር ህክምና) ፣ ቀዶ ጥገና ፣ ኢሚዩኖቴራፒ ፣ ሆርሞንቴራፒ ፣ ስቲም ሴል ትራንስፕላንት ።

 በዶ/ር ኤርሚያስ ማሞ