6 አሳሳቢ የጡት ካንሰር ምልክቶች

የጡት ካንሰር በአለማችን ቁጥር አንድ ሴቶችን የሚገድል ካንሰር ነው። በሀገራችን በርካታ ሴቶች የዚህ በሽታ ተጠቂ ሲሆን አብዛኞቹ ከግንዛቤ እጥረት የተነሳ ዘግይተው ወደ ጤና ተቋም ይሄዳሉ። በዚህም የተነሳ መዳን የሚችሉ ብዙዎች ለህልፈት ይዳርጋሉ።

እነዚህን ስድስት ምልክቶች ጠንቅቆ ማወቅ ከመዘግየት ይታደጋል። በመሆኑም ተገቢውን ህክምና በጊዜ በማግኘት ራስንም ሆነ ቤተሰብን ከካንሰር ለማዳን ይረዳል።
 
1 እባጭ፣ ይህ ዋነኛና ተቀዳሚ ምልክት ሲሆን በጡት ላይ የሚገኝ ማንኛውም እባጭ ካንሰር  አለመሆኑ  በናሙና ጥናት  መረጋገጥ  አለበት።  ነገር ግን ሁሉም እባጭ ካንሰር አይደለም።

2 የብብት ንፍፊት/ እባጭ፣ ሴቶች ብብታቸው ላይ እባጭ ካለ በሐኪም መመርመር ይኖርባቸዋል። አንዳንድ ሰዎች ላይ የጡት ካንሰር መጀመሪያ የሚታወቀው ከብብት እባጭ ነው።

3 የጡት መጠን መጨመር ፣ ይህም በውስጡ እባጭ ስላለው ሊሆን ይችላል። በመሆኑም የጡት መጠን በተለይ በአንድ በኩል ብቻ ከተለቀ እንዲሁም ቅርፁ ከተዛባ ሀኪም ማማከር ያስፈልጋል።

4 የጡት ቆዳ የብርቱካን ልጣጭ ከመሰለ ፣ ከታች በምስሉ የምትመከቱትን አይነት የጡት ቆዳ ካጋጠመ በቶሎ ምርመራ ይፈለጋል።

5 የጡት ጫፍ ወደ ውስጥ መሰርጎድ እና ያልተለመደ ፈሳሽ ማምጣት። በተለይ ድሮ ያልነበረ የጡት ጫፍ ወደ ውስጥ መግባትና ደም የቀላቀለ ፈሳሽ ማምጣት በአፋጣኝ ምርመራ ይፈለጋል።

6 የጡት ቆዳ የሚፈረፈርና የሚቆስል ከሆነ።  በተለይ በተደጋጋሚ ለኢንፌክሽን ታክመው አልድን ካለ።

ዶ/ር ሸምስ