በለጋ እድሜ ላይ ያሉ ህፃናት ጆሮዋቸውን መጎተት ከውስጥ ጆሮ ኢንፌክሽን (Otitis Media) አንዱ ምልክት ነው። የጆሮ ኢንፌክሽን በአብዛኛው በባክቴሪያዎችና በቫይረሶች አማካኝነት ይከሰታል።
.
እስከ 80 በመቶ የሚሆኑት ህፃናት የ3ኛ አመት ልደታቸውን ከማክበራቸው በፊት ቢያንስ አንድ ጊዜ በዚህ ችግር እንደሚጠቁ ጥናቶች ይጠቁማሉ።
.
እነዚህ ለጋ ህፃናት ያልዳበረ የበሽታ መከላከያ ስርአት ስለሚኖራቸውና እንዲሁም ኢስታችያን ቲዩባቸው (ጆሮን አአፍና አፍንጫ ጋር የሚያገናኝ ቱቦ) አግድም የሆነ በመሆኑ በተደጋጋሚ ለዚህ ችግር ይጋለጣሉ።
.
ሌሎች አጋላጭ የሆኑ ነገሮች
-አስተኝቶ ልጅን ማጥባት
-የእንጀራ እናት ጡጦን አብዝቶ መጠቀም
-የጣሳ ወተት መጠቀም
-በደይኬር ውስጥ መዋል
-በጉንፋን ህመም መያዝ እና የመሣሠሉት ናቸው።
.
የጆሮ ኢንፌክሽን ምልክቶች
-ጆሮን መጎተት
-የጆሮ ህመም
-መነጫነጭ
-ትኩሳት
-ከጆሮ መግል ወይም ፈሳሽ መውጣት
- ትውከትና ተቅማጥ
-ማልቀስ
-በኦቶስኮፕ (ጆሮን በሚያሳይ መሣሪያ) የታምቡር ማበጥ መቅላት እንዲሁም ፈሳሽ መውጣት ሊታይ ይችላል።
.
ወላጆች እነዚህን ምልክቶች ካስተዋሉ በቶሎ ወደ ሀኪም ቤት በመውሰድ ልጃቸውን ማሣከም አለባቸው። ህፃናትን የመጀመሪያዎቹን 6 ወራት ጡት ብቻ ማጥባት፣ ማስከተብ ፣ እንዲሁም ንፅህናን መጠበቅ የጆሮ ኢንፌክሽንን ለመከላከል ይጠቅማሉ።
.
በጊዜ ያልታከመ የጆሮ ኢንፌክሽን ለታምቡር መቀደድና ለማጅራት ገትር ለመስማት ችግር ሊዳርግ ስለሚችል ህክምናን በተገቢው ሰአት ማግኘት አለባቸው።