"የህጻናት አስም"

- አስም ምንድን ነው?
አስም የመተንፈሻ አካላችን ባእድ በሆኑ የትንፋሽ አለርጅ ቀስቃሽ ኬሚካሎች ተጽእኖ ከሚገባው በላይ በድንገት ለተወሰነ ጊዜ መጥበብ ነው። ይህ የአየር ቧንቧ ጥበት መድሀኒት ሲዎስዱ ወደ ነበረበት በቀላሉ ሊስተካከል የሚችል ነው።
ምክንያተ መንስኤ
ዋና ምክንያቱ ተፈጥሯዊ ፣ከባቢያዊ እና ቀስቃሽ በሆኑ ምክንያቶች ይነሳል። የሚፈጠረው መስተጋብር አየር ባንቧን ለዘለቀ ቁስለት/ብግነት በማጋለጥ አለርጅ ቀስቃሽ ሽታዎች ሲኖሩ የአየር ቧንቧ ከልክ ያለፈ ተለዋጭ ጥበት እና የቆሸሸ አየር ከሳንባ በሚፈለገው ልክ አለመውጣት ሳል እና የመታፈን ምክንያትን ያመጣል። ከባቢያዊ እና ቀስቃሽ ምክንያቶችን መቀነስ ይቻላል።
.
- የአስም አይነቶች
1. በተደጋጋሚ የሚነሳ አስም/recurrent asthma/seasonal ይህ ወቅታዊ ሁኔታዎች የሚያስነሱት አስም ነው። ቀስቃሽ ምክንያቶችን በመቀነስ ድግግሞሹን መቀነስ እና ደረጃውንም መቆጣጠር ይቻላል።
2. ረጅም ጊዜ የቆየ አስም /chronic asthma ለረጅም ጊዜ የዘለቀ አስም
.
- አለርጅ/አስም ቀስቃሾች ምንድን ናቸው?
1. የሲጋራ ፣ የከሰል እና የማገዶ ጭስ
2. የአበባ፣ቆሻሻ፣ የፅዳት መጠበቂያ/ዴቶል/ ፣ የሽቶ እና ላበት ማጥፊያዎች ሽታ
3. ላባ እና ጸጉር ያላቸው የቤት እንስሳት
4. የከብቶች ሽንት እና አዛባ
5. በረሮ የሚረጨው ኬሚካል
6. እርጥበት እና ቅዝቃዜ ያለው ስፍራ
.
7. የጉንፋን ቫይረስ
8. የኬሚካል ሽታ
9. ጭንቀት እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ
10. ሻጋታ
11. የጨጓራ አሲድ ቅርሻ/Gastro esophageal reflux disease
12. የአፍንጫ አለርጅ እና ሳይነስ ህመም
.
- ለአስም አጋላጭ ሁኔታዎች
1. የቆዳ አለርጅ/የቆዳ አስም
2. የአፍንጫ እና አይን አለርጅ
3. የምግብ አለርጅ
4. አስም ያለበት እናት ፣ አባት ፣ እህት ወይም ወንድም
5. ከጉንፋን ጋር የማይያየያዝ ሳል
.
- የህመም ምልክቶች
1. በቅዝቃዜ ወቅት እና ማታ ማታ የሚባባስ ደረቅ ሳል
2. የደረት መጨነቅ/የመታፈን ስሜት
3. የትንፋሽ መፍጠን
4. የድካም ስሜት
5. የሰውነት መዛል እና ላበት
6. ሙዚቃዊ ትንፋሽ
7. ራስ ምታት፣ የትኩረት መቀነስ፣ እና አቅልን መሳት
.
- አስም አመላካች ነገሮች ምን ናቸዉ
1. በጥርጣሬ የአስም መድኃኒት ሲሰጥ በቶሎ የሚሻል ከሆነ
2. ወላጅ አስም ወይም አለርጅ ካለበት
3.ነባር የትንፋሽ አለርጅ ካለ
4. ተደጋጋሚ የመተንፈሻ አለርጅ:
.
- ህጻናት ላይ አስም ይምንለው በአመት ውስጥ ሶስት ጊዜ እና ከዚያ በላይ የሆነ
ሀኪም ያረጋገጠው የመተንፈሻ አለርጅ ካለ ነው።
.
- አስምን በምን እናረገግጣለን
1. የሳንባ ምርመራ:
በጤንነታቸው ወቅት ያላቸው የሳንባ አየር የማስገባት እና የማስወጣት
የመጨረሻ አቅም ጋር ሲነጻጸር ምን ያህል በህመሙ ምክንያት ቀነሰ የሚለውን
በመለካት።
2. የአየር ቧንቧ ለትንፋሽ ቧንቧ አስፊ ህይዎት አድን መድሀኒት ያለውን ፈጣን
ምላሽ በማየት።
3. በአለርጅ አምጭ/ቀስቃሽ መድሃኒት አስም የመከሰት እድሉን መሞከር(ይህ
ምርመራ ብዙ አይመከርም)
4. በእስፓርታዊ እንቅስቃሴ ያለውን የተቃጠለ አየር የማስውጣት አቅም
በመለካት።
.
- የአስም ህክምና
1. የአየር ቧንቧን ጥበት የሚያስተካክሉ መድሀኒቶች
2. የአየር ቧንቧ ቁስለትን/ብግነትን የሚቀንስ መድሃኒት
3. አለርጅን የሚቀንስ መድሃኒት
4. አስም ቀስቃሽ የሆነውን ህመም ማከም
5. ቤትን ከአስም ቀስቃሽ የሆኑ ነገሮች ነጻ በማድረግ አስም እንዳይነሳ
መከላከል
6. በቅዝቃዜ እና ጉንፋን በሚበዛባቸው ወቅቶች የአስም ቅድመ መከላከል
መድሃኒት መስጠት
.
- እንደ መውጫ
የህጻናት የመተንፍሻ ቱቦ በተፈጥሮ ጠባብ በመሆኑ ምክንያት አስም ጋር
የሚመሳሰሉ ብዙ ህመሞች ስላሉ አስም አለ የምንለው በታፈኑ ወቅት በአስም
መድሀኒት ያላቸው ለውጥ አመርቂ ከሆነ እና ለአስም ተጋላጭነት ካላቸው ነው።
.
እድሜያቸው ከ4 ዓመት በታች ለሆኑ ህጻናት የሳንባን በአግባቡ መስራት ወይም
አለመስራት ለማወቅ ለምርመራ እድሜያቸው ስለማይፈቅድ በብዛት በክትትል
ብቻ ነው መለየት የሚቻለው። አካባቢያዊ አስም ቀስቃሽ ሁኔታዎችን
በማስተካከል አስምን መከላከል ዉጤታማ ነው።