የጤና ሚኒስትር ዶ/ር አሚር አማን በድሬደዋ ከተማ አስተዳደር የችኩንጉንያ ወረርሽኝን ለመቆጣጠር በጤና ሚኒስቴር እና በክልሉ ጤና ቢሮ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል::.
ሚኒስትሩ ከድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፣የጤና ቢሮ ሀላፊዎች ፣ ባለሙያዎች እና ሌሎች የከተማው ከፍተኛ አመራሮች ጋር በመሆን በበሽታው ተይዘው በጤና ተቋማት ህክምና እየተደረገላቸው ያሉትን ወገኖች እንድሁም በህብረተሰቡ ውስጥ በመኖሪያ ቤትና አከባቢው በሽታውን ለመከላከል እየተሰራ ያለውን ስራ ተመልክተዋል::
የጤና ሚኒስቴር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ወረርሽኙን ለመቆጣጠር በቁርጠኝነት እንደሚሰራ ገልጸው ውሃ የሚያቁሩ ጉድጓዶችን የመድፈን፣ ማፋሰስና ኬሚካል ርጭት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አስገንዝበዋል:: በከተማው እስካሁን ሃያ ዘጠኝ ሺህ( 29,000) ሰዎች በበሽታው የተያዙ ሲሆን የሞተ ያለመኖሩን ማረጋገጥ ተችሏል::